AM/Prabhupada 0010 - ክርሽናን ለማስመሰል አትሞክሩ፡፡



Lecture on SB 7.9.9 -- Mayapur, February 16, 1976

የክርሽና: እነዚህ 16000 ባለቤቶች: እንዴት ባለቤቱ ሊሆን ቻሉ? ታሪኩንም ታውቁታላችሁ: 16000 በጣም የሚያምሩ ነበሩ:: ማለቴም: የነገስታት ልጅአገረዶች ሁሉ: በክፉ ስይጣናዊ ታፍነው ተወስደው ነበር:: የዚህስ ክፉ ሰው ስሙ ማን ነበር? "ብሆማአሱራ" ነበር:: እነዚህም ልእልቶች: ለጌታ ክርሽና "በዚህ መጥፎ ታፍነን ተወስደን በስቃይ ላይ ነው ያለነው እና: እባክህ ከዚህ ፈተና አድነን" ብለው ፀሎት አደረጉ:: ስለዚህም ጌታ ክርሽና: ሊያድናቸው መጣ:: ብሆማሱራም ተገድሎ: ልጅ አገረድ ልዕልቶቹ ሁሉ ነፃ ሊወጡ ቻሉ:: ነጻ ከወጡ በኋላም መንገድ ሳይቀጥሉ: እዚያው ቆመው ቀሩ:: ጌታ ክርሽናም እንዲህ አላቸው: "አሁን ወደ ቤት: ወደ አባታችሁ መሄድ ትችላላችሁ አላቸው::" እነርሱም "አንዴ ታፍነን ተወሰደን ስለነበረ: አሁን ሊያገባን የሚችል የለም" ብለው ተናገሩ:: በህንድ አገር ውሰጥ: አሁንም በአንዳንድ ቤተሰብ: ይህ መመሪያ አለ:: አንድ ልጅ አገረድ: ለአንድ ወይንም ለሁለት ቀን: ከቤትዋ ውጪ ካደረች: የሚያገባት ሰው አይኖም:: የሚያገባት ሰው አይኖም:: ምክንያቱም ተደፍራ ይሆናል ተብሎ ስለሚገመት ነው:: በህንድ አገር ይህ መመሪያ አሁንም አለ:: እነዚህም ልእልቶች ለብዙ ቀን እና ለብዙ አመታት ተይዘው ነበር:: ልእልቶቹም አባቶቻችን እንኳን ሊቀበሉን አይችሉም: ብለው: ለክርሽና አማፀኑት:: ማንም ሰው ሊያገባንም አይስማማም ብለው ተናገሩ:: ክርሽናም ሃሳባቸውን ተረዳላቸው: ያሉበትም ደረጃ: የቀና አለመሆኑንም ተረዳላቸው:: በክርሽና ይፈቱም እንጂ: የሚሄዱበት ግን የላቸውም:: ከዚህም ክርሽና: እንደ ደግነቱ "ብሃክታ ቫትሳላ" እንዲህ ጠየቃቸው "ምን ማድረግ ትፈልጋላችሁ?" እነርሱም እንዲህ አሉ: "አንተ እራስህ ካልተቀበልከን በስተቀር: ሌላ ቦታ የምንሄድበት ቦታ የለንም" ብለው ተናገሩ:: ክርሽናም ወዲያውኑ "እሺ እንሂድ አላቸው" ይህ ጌታ ክርሽና ነው:: እነዚህም 16000 ልእልት ሚስቶቹም በአንድ ካምፕ ውስጥ ታጉረው አልተቀመጡም:: ክርሽና ወዲያውኑ 16500 ቤተ መንግስቶች ገነባ:: ሁሉንም እንደ ሚስቶቹ ስለተቀበላቸውም: እያንዳንዳቸውን እንደሚስት ሊንከባከባቸው ወሰነ:: መሄጃ የላቸውም ብሎም አስቦ ሳይሆን: እንደ ንግስቶች በክብር ሊንከባከባቸው አሰበ:: እንዲሁ ላስጠጋቸው ብሎ ብቻ አላሰበም:: በክብር: እንደ ንግስቶች: እንደ ክርሽና ንግስቶች: ለከባንከባቸው አሰበ:: እንዲህም አሰበ "16000 ንግስቲት ባለቤቶቼ" እኔ ብቻዬን ከሆንኩ ግን እንዴት እያዳንዳቸው ሊያገኙኝ ይችላሉ ብሎም አሰበ:: ብቻዬን ከሆንኩኝ: እያንዳንዳቸው 16000 ቀናት መቆየት ሊኖርባቸው ነው:: ይህንንም በማሰብ ጌታ ክርሽና 16000 ጌዜ እራሱን ለማባዛት ወሰነ:: ይህ ጌታ ክርሽና ነው:: እነዚህ ተንኮለኛ ሰዎች ግን: ክርሽና ሴቶች ጠላፊ ነው ብለው ያሙታል:: ክርሽና እንደኛ አይደለም:: እኛ አንድ ሚስት እንኳን ለማስተዳደር ያዳግተናል:: ጌታ ክርሽና ግን 16000 ሚስቶች ይዞ በ16000 ቤተመንግስት ውስጥ ለማስተዳደር ይችላል:: እራሱንም ለእያንዳንዷ ንግስት አባዝቶ አንድ በአንድ ለማስተዳደር ይችላል:: በዚህም መንገድ እያንዳንዷን ንግስት ለማስደሰት በቃ:: ይህ ጌታ ክርሽና ነው:: የክርሽናን ማንነት በዚህ መንገድ መረዳት እንችላለን:: ክርሽናን ለመምሰል መሞከር የለብንም:: በመጀመሪያ ደረጃ የክርሽናን ማንነት መረዳት አለብን::