AM/Prabhupada 0018 - የሎተስ እፅዋት በመሰለው የመንፈሳዊ አባት እግር እምነት ማድረግ፡፡



Lecture on SB 6.1.26-27 -- Philadelphia, July 12, 1975

ፕራብሁፓዳ እንዲህ አለ: "ይህንን ግዜያችንን መፍትሄ ለማግኘት መጠቀም አለብን" መፍትሄ የሚያስፈልገውም: ለዚሁ በተደጋጋሚ: ለሚወለደው እና ለሚሞተው ህይወታችን ነው:: ታድያ ይህ መፍትሄ: ወደ ትክክለኛ መንፈሳዊ አባት (ጉሩ)ሳይሄዱ:እንዴት ለመረዳት ይቻላል? ስለዚህም “ሻስትራ” (ቅዱስ መጽሃፍ)እንዲህ ይላል “ታድ ቪግናናርትሃም” የሕይወታችሁን ዋናውን ችግር ለማወቅ ከፈለጋችሁ እና: የክርሽና ንቃትን በደንብ ለመረዳት ከፈለጋችሁ: ህይወታቹህ እንዴት ዘላለማዊ መሆን እንደሚችል እና እንዴት ወደ የመጣንበት የአማላካችን ቤት ለመመለስ ማወቅ ከፈለጋችሁ: የመንፈሳዊ አባት “ጉሩ” መቅረብ አለባችሁ: ታድያ ማነው ይህ “ጉሩ”?ይህ በቀላሉ እንዲረዱት ተደርጓል: ጉሩ የራሱን ሃሳብ እንዲህ እያለ አይፈጥርም “ይህንን አድርግ:ገንዘበ ስጠኝ እና:ደስተኛ:ትሆናለህ” ይህ ጉሩ አይደለም:ይህ ለይት ያለ ገንዘብ መሰብሰቢያ ጥበብ ነው: ይህ በሻስትራ “ሙድሃ” (ሞኝ)ብሎ ተጠቅሷል:በእንደዚህ አይነት መንገድ ብዙ ሰው በሞኞች ገነት ውስጥ:ተሰብስበው ይገኛሉ: ልክ እንደ አጃሚል: የራሱን ሃሳብ የሚፈጥር ማለት ነው “ይህ የኔ ስራ ነው” ብሎ የራሱን መንፈሳዊ ሃላፊነት የሚወስድ: የህ ሞኝ ሰው ነው: የመንፈሳዊ ተግባራችሁን መረዳት ያለባችሁ ከጉሩ ነው: እንዲህ እያልንም በቀን በቀን እንዘምራለን :“ጉሩ ሙክሃ ፓድማ ቫክያ:ሲቴቴ ኮሪያ አይካ:አራና ኮሪሆ ማኔ አሳአ” እንዲህ ነው ሕይወታችን መመስረት ያለበት:“ጉሩ ሙክሃ ፓድ” ለትክክለኛ ጉሩ አንደበታችሁን ሰጥታችሁ: የተቀበላችሁትን ትእዛዝ ፈጽሙ: ያን ግዜ ሕይወታችሁ የተሟላ ይሆናል:“አራ ና ኮሪሆ ማኔ አሳአ” አንተ ተንኮለኛ የሆንክ ሰው: ሌላ ምንም ነገር አያስፈልግህም: በቀን በቀን ትዘምራለህ:ትርጉሙን ግን ትረዳዋለህን? ወይስ ዝም ብለህ መዘመር ብቻ ነው? ትርጉሙስ ምንድን ነው? ማንስ ያስረዳሃል?ማንም አያውቅምን? አዎ:ትርጉሙ ምንድን ነው? አገልጋይም እንዲህ አለ:”የእኔ ምኞት አእምሮዬ ንጹህ እህዲሆን ነው“ “ይህም ከመንፈሳዊ አስተማሪዬ ከአፉ ከሚወጡት ቃላቶችን በማዳመጥ ነው” ”ከዚህም ሌላ ምንም የምፈልገው ነገር አይኖ ርም“ ፕራብሁፓዳም እንዲህ አለ:”ይህ ትክክል ነው!ትእዛሱም ይህ ነው “ጉሩ ሙክሃ ፓድማ ቫክያ ሲቴቴ ኮሪያ አይካ” “ቺታ” ማለት ህልውና ወይንም ልቦና ማለት ነው “ይህንን ብቻ አደርጋለሁ! አለቀ!” “የእኔ ጉሩ ማሃራጅ እንዲህ ስለአለኝ: እንዲህ አደርጋለሁ” “ሲቴቴ ኮሪያ አይካ አራ ና ኮሪሆ ማነ አሳአ” ይህ የእኔ ትእቢት አይደለም:ይህን ተግባር የምፈጽመው ትእዛዝን በመከተል ነው: ከመንፈሳዊ ወንድሞቼ ትንሽ ለየት ያለ እርምጃ ብታዩብኝም:ይሄ ትእዛዙን ስለተከተልኩ ነው: እኔ አቅም የሌኝም:ነገር ግን የመንፈሳዊ አስተማሪዬን (ጉሩ) ቃላቶች እንደ ሕይወቴ እና ነፍሴ ወስጀዋለሁ: ይህም እውነት ነው:“ጉሩ ሙክሃ ፓድማ ቫክያ:ሲቴቴ ኮሪያ አይካ” ሁሉም ይህን ፈለግ መከተል ያስፈልገዋል:ነገርግን ከትእዛዙ ውጪ መጨመር እና መቀየር ከጀመረ:ወድቀት ያመጣል: ከትእዛዝ ውጪ መጨመር እና መቀየር አያስፈለግም: ጉሩን መቅረብ ያስፈለጋችኋል:ጉሩ ማለት የአምላክ ክርሽና ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው: ለማገልገልም የክርሽናን ትእዛዝ ተቀብሎ ይፈጽማል: እንደዚህም ሰው ውጤታማ ደረጃ ይደርሳል: “እኔ ከጉሩዬ በላይ አወቂ ነኝ” ብላችሁ ትእቢት ካደረባችሁ ግን: “እንደ ፈለግሁ በትእዛዙ ላይ መጨመርም መቀየርም እችላለሁ” ብለን ካሰብን:ውድቀት ያመጣብናል: ይህ ብቻ ነው ትርፉ:አሁን መዝሙሩን ቀጥል: አገልጋይ:“ሽሪ ጉሩ ቻራኔ ራቲ:ኤይ ሴ ኡታማ ጋቲ” ፕራብሁፓዳ: “ሽሪ ጉሩ ቻራኔ ራቲ ኤይ ሴ ኡታማ ጋቲ” ትክክለኛ የመንፈሳዊ እርምጃ ማድረግ ከፈለጋችሁ:ወደ ጉሩ እግር በእምነት መጠጋት አለባችሁ:ከዚያስ? አገልጋይ:“ጀ ፕረሳዴ ፑሬ ሳርቫ አሳአ” ፕራብሁፓዳ: “ጀ ፕራሳዴ ፑሬ ሳርቫ አሳአ:ያስያ ፕራሳዳት” የሁሉም ይቫይሽናቫ ትእዛዝ ይህ ነው! ይህንን ካልተከተልንም: ሞኝ ሁነን እንቀራለን!ይህም በ “አጃሚል ኡፓክያና” ተገልጧል: ዛሬ ይህንን ጥቅስ እያነበብን ነው:“ሳ ኤቫም ቫርታማናህ አግናህ” እንደገናም እንዲህ አለ: እንደገና ቭያሳዴቭ እንዲህ አለ: “ይህም ተንኮለኛ ናራያን በተባለው ልጁ ስራ ተመስጦ ነበር” የናራያናን ማንነትም በደንብ አላወቀም: ልጁን ግን በደንብ ያውቃል: ታሞ በሞት ላይ እያለም የልጁን ስም ናራያናንም ደጋግሞ ይጠራ ነበር: “ናራያን እባክህ ወደ እዚህ ቅረብ:እባክህ ወደ እዚህ ቅረብ ይህን ውሰድ” ክርሽናም የእራሱን ስም ናራያናን በመጥራቱ ምህረቱን ሊያሳየው ፈለገ: ጌታ ክርሽና ምህረት አውራጅ ነው: አጃሚል ወደ ናራያን ለመሄድ ፈልጎ አልነበረም ናራያናን ይጠራ የነበረው: ልጁን በጣም ስለሚወደውም ነው ይጠራው የነበረው: በዚህ አጋጣሚግን:የክርሽናን ቅዱስ ስም “ናራያን”ን ለመጥራት በቃ: ይህም የአጃሚል ጥሩ እድል ሆነ:በዚህም ምክንያት በመንፈሳዊ አለም ስማችንን ወደ መንፈሳዊ ስም እንቀይረዋለን: ለምን?እያንዳንዱ ስማችን የጌታ ክርሽና አገልጋይ መሆናችንን የሚያንፀባርቅ መሆን አለበት: ልክ “ኡፔንድራ” እንደማለት: ኡፔንድራ ማለት ቫማናዴቭ ማለት ነው: እንዲሁም ሁሉ “ኡፔንድራ ኡፔንድራ” ብላችሁ ብትጣሩ:ይህ የመንፈሳዊ ስም ጥሩ በረከትን ያመጣላችኋል: ይህም ወደ በኋላ ተተንትኖ ይገለጽላችኋል: