AM/Prabhupada 0037 - ክርሽናን የሚያውቅ ሁሉ እንደ ጉሩ ወይንም መምህር ይቆጠራል፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Hong Kong, January 25, 1975

እና እንዴት አድርገን ነው የብሃገቫንን (ፈጣሪ) ሃይልን መረዳት የምንችለው? እንዴትስ አድርገን ነው የመፍጠር ሃይሉን ለመረዳት የምንችለው? የብሃገቫንስ (ፈጣሪ) ኃይሉ እና ችሎታው ምንድን ነው? እንዴት ነው የሚያደርገው? እንደዚህም ጠይቆ ሁሉን ነገር ማወቅ: ይሄ ራሱ ሳይንስ ነው:: ይህ የክርሽና ሳይንስ ነው:: "ክርሽና ታትቫ ግያን" "ዬ ክርሽና ታትቫ ቬታ ሴይ ጉሩ ሆይ" (ቼቻ ማድህያ 8 128) ቼያታንያ ማሃፕራብሁ እንዲህ ይላል: "ማን ነው ጉሩ ማለት?" ጉሩ ማለት: "ዬ ክርሽና ታትቫ ቬታ ሴይ ጉሩ ሆይ" ክርሽናን በትክክል የሚረዳ ሁሉ ጉሩ ነው: ጉሩ በቀላሉ ሊመረት አይችልም:ጉሩ መሆን ያለበትም ግን: ማንም ሰው ክርሽናን በደንብ የተረዳ ከሆነ ነው: በቀላሉ ግን ክርሽናን ማወቅ አንችልም:ክርሽናንም መቶ በመቶ ለማወቅ አንችልም: የክርሽና ሃይሎች በጣም የተለያዩ እና ብዙ ናቸው: “ፕራሻያ ሻክቲር ቪቪድሃቫ ሽሩያቴ (ቼቻ ማድህያ 13 65 የትርጉም ፍቺ) አንዱ የአምላክ ሃይል በአንድ በኩል ሲሰራ:ሌላው ሃይሉ ደግም በሌላ በኩል ይሰራል: ቢሆንም ግን ሁሉም የአንድ አምላክ ሃይሎች ናቸው: ”ፓራሽያ ሻክቲር ቪቪድሃይቫ ሽሩያቴ:ማያድህያክሼና ፕራክርቲህ ሱያቴ ሳቸራቸራም“ (ብጊ:9 10) ይህ ”ፕራክርቲ“ ይህ አበባ በተፈጥሮ ሲበቅል እናየዋለን: አበባ ብቻ ሳይሆንም: ብዙ ተክሎች ከዘር ሲበቅሉ እናያለን: ከጽጌረዳ ዘር የጽጌረዳ ተክል እናገኛለን:ከቤላ ዘር የቤላ ዛፍ እናገኛለን: ይህ ሁሉ እንዴት ነው የሚከናወነው? አፈሩ አንድ ነው:ውሃው አንድ ነው:ዘሮቹም ይመሳሰላሉ: ግን ሲያድጉ:የተለያየ ባህርይ ይዘው ያድጋሉ:ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህም እንዲህ ይባላል:”ፓራስያ ሻክቲር ቪቪድሃይቫ ሽሩያቴ ስቫብሃቪኪ ግያና“ ተራው ሰው:ወይንም ሳይንቲስቶች:“ይህ ያደገው በተፈጥሮ አማካኝነት ነው” ይላሉ: ነገር ግን ተፈጥሮ ምን እንደሆነ አይረዱም:ማነው የተፈጥሮን ሂደት የሚቆጣጠረው? ይዚህ የአለማችን ተፈጥሮ:እንዴት ነው የሚሰራው? ይህም በብሃገቨድ ጊታ ተገልጿል:”ማያ ድያክሼና“ (ብጊ 9 10) ክርሽናም እንዲህ ይላል:”በእኔ ቁጥጥር ስር:ይህ ተፈጥሮ ይንቀሳቀሳል“ ይህ ነው የፍጹም ገለጻው:ተፈጥሮ:ንጥረ ነገር:እራሱ ሊቀላቀል እና ሊያመርት አይችልም: እነዚህ ታላላቅ ህንፃዎች:የተሰሩት በንጥረ ነገሮች ነው: ነገር ግን ንጥረ ነገሮችን በራሳቸው ህንፃ ለመሆን አልበቁም:ይህ ሊሆን የማይችል ነገር ነው: ነገር ግን: አንድ ትንሽ:ረቂቅ የሆነ:ነፍስ:ኢንጂኔሩ ወይንም አርክቴክቱ ነው:እዚህ እንዲደርስ ያደረገው: እርሱም ነው:ንጥረ ነገሮችን ተጠቅሞ አሳምሮ ትልቅ ህንጻ ለመስራት የበቃው: ይህንን ነው እኛ በተግባር ያየነው: ታድያ እንዴት ብለን ነው ይህ ተፈጥሮ አውቶማቲካሊ ያለ ተቆጣጣሪ ሊሰራ የሚችለው? ተፈጥሮ እራሱ አውቶማቲካሊ ሊሰራ አይችልም:ከፍተኛ ተቆጣጣሪ አእምሮ ያስፈልገዋል:ከፍተኛ ሸማኔ ያስፈልገዋል:ስለዚህም ተፈጥሮ ከፍተኛ የአማላክ ትእዛዝ ያስፈልገዋል: በዚህ አለም ላይ እንደምናየውም ሁሉ:እኛም ትልቅ የተደራጁ ነገሮች እናያለን:ፀሃይ እና የፀሃይ እንቅስቃሴ: የሙቀቱን ሃይል:የፀሃይ ብርሃንን ሃይል: እናያለን ይህስ እንዴት ነው በጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው?ይህም በሻስትራ ተጠቅሷል: ”ያስያግናያ ብህራማቲ ሳምብህርታ ካላ ቻክሮ ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሃም ብሃጃሚ“ የምናያት ፀያይም እንደ ምንኖርባት ምድራችን ፕላኔት ናት: በዚህ ምድር ላይ ብዙ ፕሬዚደንቶች ሲመሩ መቆየታቸውን ብናውቅም:በቀድሞ ግዜ ግን አንድ ፕሬዚደንት ወይንም የምድር መሪ ነበር: እንደዚሁም ሁሉ በየአንዳንዱ ፕላኔቶች አንድ ፕሬዚደንት ወይንም መሪ አለ: በፀሃይ ፕላኔትም ላይ ይህ ብሃገቨድ ጊታ ለመጀመሪያ ተገለፀ: ክርሽናም እንዲህ ይላል:”ኢማም ቪቫሽቫቴ ዮጋም ፕሮክትቫን አሃም አቭያያም“ (ብጊ 4 1) ”በመጀመሪያ ግዜ ይህንን የብሃገቨድ ጊታ ሳይንስን ያስተማርኩት ለቪቫሽቫን ለፀሃዪ ንጉስ ነው“ ቪቫሽቫን ማለት የፀሃይ ንጉስ ወይንም ፕሬዚደንት ማለት ነው:ልጁም ደግሞ ማኑ ይባላል: ይህ የአሁኑ ግዜአችን የእርሱ ግዛት ግዜ ነው: ይህ ዘመን የቫይቫሽቫታ ማኑ ዘመን ይባላል: ቫይቫሽቫታ ማለትም ከቪቫሽቫን የመጣ ወይንም የቪቫሽቫን ልጅ ማለት ነው:የሚባለውም ቫይቫሽቫታ ማኑ ነው: