AM/Prabhupada 0059 - ትክክለኛ ስራችሁን አትዘንጉ፡



Lecture on BG 2.14 -- Mexico, February 14, 1975

ጥያቄውም እምዲህ ነው:“እኔ (ነፍሴ)ዘለአለማዊ ከሆንኩ:ለምንድን ነው ህይወት ብዙ ስቃይ የተሞላባት?” ለምንስ በግድ እንድሞት ተገደድኩ? ይህ የአዋቂ ሰው ጥያቄ ነው:“እኔ ዘለአለማዊ ከሆንኩኝ” “ለምን እዚህ አለማዊ ገላ ውስጥ:የሚሞት:የሚወለድ:የሚያረጅ እና የሚታመም:ገላ ውስጥ:ለምን ተወለድኩ?” ስለዚህ ክርሽና እንዲህ ያስረዳናል:“ይህ የስቃይ ኑሮ የሚቀያየርብን:ይህን የአለማዊ ገላ ይዘን ስለተወለድን ነው:” እነዚያም “ካርሚ” የሆኑት:ማለትም በስሜታዊ ደስታ ግዜያቸውን የሚያጠፉ: ”ካርሚ“ ይባላሉ: ካርሚዎች:ስለ ወደፊት ህይወት ምንም ግድ አይሰጣቸውም:ፍላጎታቸውም: የዚህን ኑሮ የሚያመቻች ነገሮችን ለማግኘት ብቻ ነው: ልክ እንደ ልጅ:ለወላጆቹ ግድ ሳይሰጥ:ሙሉ ቀን ሲጫወት ይኖራል: ለወደፊት ስለአለው ኑሮም ግድ አይሰጠውም:ትምህርትም ለመከታተል ግድ አይሰጠውም: ነገር ግን:በሰው ልጅ ህይወት ላይ እያለን:አዋቂ ሰዎች ከሆንን: ጥረት ማድረግ የሚገባንም:የመሞት:የመወለድ:የማርጀት እና የመታመም ችግር የሌለበትን ህይወት ለማግኘት ነው: ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበራችን:ይህንን ለማስተማር ነው የተቋቋመው: አሁን አንዱ እንደዚህ ሊል ይችላል:”ህይወቴን ለክርሽና ንቃት ሰጥቼ ባገለግል“ ”ምን ያህል ለመኖር የሚያስፈልገኝን ነገር ማግኘት እችላለሁ?“ መልሱም በብሃገቨድ ጊታ ተገልጿል:”ማንም ሰው በክርሽና ንቃት በማገልገል ላይ የሚገኝ“ የሚያስፈልገውን ነገር በሙሉ ክርሽና ያቀርብለታል: ክርሽና ለሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ነገር በሙሉ እያቀረበ ይገኛል: ”ኤኮ ዮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን“ ያም አንድ አምላክ እና ፈጣሪ:ህይወት ላላቸው ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን እያቀረበ ይገኛል: ስለዚህም ለክርሽና አገልጋይ:ወደ መጣበት ቤቱ ወደ ፈጣሪ ዘንድ ለመመለስ ለሚያስበው:ምንም እጥረት አይኖርበትም: በብሃገቨድ ጊታ:ክርሽና በእኔ ተማመኑ ብሏል “ቴሻም ሳታታ ዩክታናም ዮጋ ክሴማም ቫሃሚ አሃም” (ብጊ10 10 ) “የእኔ አገልጋይ ሁልግዜ በእኔ አገልግሎት ላይ ይገኛል” “የህይወቱንም አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ አቀርብለታለሁ” በተግባር የተሰራም ምሳሌ ለማሳየት ከተፈለገ:በእኛ በክርሽና ንቃተ ማህበር:አሁን ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ቅርንጯፎች አሉን: በየእያንዳንዱም ቤተ መቅደስ:ከ25 ያላነሱ እና እስከ 250 የሚሆኑ አገልጋዮች እየኖሩ ይገኛሉ: ቢሆንም ግን የተወሰነ ወርሃዊ ገቢ የለንም: በወርም ከ 80000 ዶላር በላይ:ለቅርንጫፎቻችን እያጠፋን እንገኛለን: ቢሆንም በክርሽና በረከት ምክንያት ምንም የጎደለብን ነገር የለም: ሁሉም ነገር ቀርቦልን ይገኛል: አንዳንድ ግዜ ብዙም ሰው በዚህ ይደነቃል:“እነዚህ ሰዎች ስራ አይሰሩም” “ሙያም አይወስዱም:ሃሬ ክርሽና ሲዘምሩ ብቻ ይገኛሉ: ታድያ እንዴት አድርገው ነው የሚኖሩት?” ብለው ይጠይቃሉ: “ድመቶች እና ውሾች በፈጣሪ ምርቃት ለመኖር የሚችሉ ከሆነ:ይሄ ጥያቄ የማያስፈልግ ነው:” “አገልጋዮች በአምላክ በረከት ተመችቷቸው እና ሁሉ ተሟልቷላቸው ለመኖር ይችላሉ” ይህም ጥያቄ የለውም:ነገር ግን:አንድ ሰው እንዲህ ቢጠይቅ:“የክርሽና ንቃቴን እየተከታተልኩ ነው” “ነገር ግን በብዙ ነገር እየተሰቃየሁ እገኛለሁ” ብሎ ቢያስብ: ለነሱም ሆነ:ለእኛ:መመሪያችን እንዲህ ነው:“ማትራ ስፓርሻስ ቱኩንቴያ:ሺቶሽና ሱክሃ ዱክሃ ዳህ” (ብጊ 2 14) “እነዚህም ስቃይ እና ደስታዎች:ልክ እንደ ክረምት እና በጋ ይቆጠራሉ” በክረምት ቀዝቃዛ ውሃው በጣም የሚያሳምም ነው:በበጋ ደግሞ በጣም ደስ ያሰኛል: ታድያ የውሃ ባህርይ ምንድን ነው?የሚያስደስት ነው ወይንስ የሚያሳምም? የውሃ ባህርይ የሚያሳምም ወይንም የሚያስደስት አይደለም:ነገር ግን እንደ ወቅቱ:ባህርዩው የለያያል: ሲነኩት:እንደ ወቅቱ:ሊያምም ይችላል ወይንም ሊያስደስት ይችላል: እነዚህም የሚፈራረቁ ደስታ እና ስቃይ እዚህ በደንብ ተገልፀዋል:“እንደ ወቅት ይመጣሉ ወይንም ይሄዳሉ:ቋሚ አይደሉም” “አጋማ አፓዪኖ አኒትያህ” ማለት “ይመጣሉ ወይንም ይሄዳሉ:ስለዚህ ቋሚ አይደሉም” ክርሽና ስለዚህም ይመክረናል “ታምስ ቲቲክስቫ ባሃራታ” ትእግስት ማድረግ አለብህ: ነገር ግን ዋናውን የክርሽና ንቃትህን መርሳት የለብህም: ሰለዚህ ለአለማዊ ስቃይ እና ደስታ: ብዙ ግድ አይስጥህ: