AM/Prabhupada 0072 - የአገልጋይ ስራ ለጌታው ልቦናውን መስጠት ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0071
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0073 Go-next.png

የአገልጋይ ስራ ለጌታው ልቦናውን መስጠት ነው፡፡
- Prabhupāda 0072


Lecture on CC Madhya-lila 20.108-109 -- New York, July 15, 1976

ማንም ሰው ቢሆን ጌታ ለመሆን አይችልም፡፡ ይህ የማይቻል ነገር ነው፡፡ ይህንም ትቅስ በቼታንያ ቻሪታምሪታ ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ”ኤካሌ ኢሽቫራ ክርሽና አራ ሳባ ብህርትያ“ (ቼቻ፡ 5.142) ጌታ ለመሆን የሚችለው ሽሪ ክርሽና ብቻ ነው፡፡ ሌሎቻችን ሁሉ አገልጋዮች ነን፡፡ ይህ ነው የእኛ ትክክለኛ ደረጃ፡፡ ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ግን ጌታ ለመሆን ስንጥር እንገኛለን፡፡ ይህም ለመኖር ያለን ትግል ነው፡፡ የማንሆነውን ነገር ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ እነዚህንም ዓረፍተ ነገሮች እናውቃለን፡፡ ”ለመኖር ትግል ማድረግ“ ”አቅም ያለው ብቻ ለመኖር ይችላል፡፡“ እንደዚህም ሁሉ ለመኖር ትግል አለ፡፡ ጌታ ለመሆን አንችልም፡፡ ቢሆንም ግን ጌታ ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በማያቫዲ ፍልስፍና ውስጥ ያሉ ሁሉም የተለያዩ ጥብቅ እና አስቸጋሪ መመሪያዎችን ሲከተሉ ይታያሉ፡፡ ዓላማቸውስ ምንድን ነው? ዓላማቸውም “ከዓብዩ ጌታ ጋር አንድ ለመሆን እፈልጋለሁ፡፡” በማለት ነው፡፡ ይህም የተመሳሰለ ስህተት ነው፡፡ ጌታ ለመሆን አይችሉም፡፡ ነገር ግን እንደ ዓብዩ ጌታ ለመሆን ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህም ማያቫዲዎች ምንም እንኳን የጠበቀ እና አስቸጋሪ መመሪያዎችን የሚገተሉ ቢሆኑም፤ ወይንም “ቫይራግያ” ሁሉንም ዓለማዊ ነገር እርግፍ አድረገው የሚገኙ ቢሆኑም፤ ዓላማው ምንድነው? የዓለማዊ ደስታቸውን ሁሉ እርግፍ በማድረግ ወደ ጫካ በመሄድ የጠበቀ ስርዓትን በመከተል መንፈሳቸውን ከፍ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ታድያ ግባቸው ምንድነው? "ከግዜ በኋላ ከዓብዩ ጌታ ጋር አንድ ለመሆን እበቃለሁ፡፡“ ማለትን ነው፡፡ ይህም እንደ ዓለማውያኖቹ የተመሳሰል ስህተት ነው፡፡ ማያ ወይንም የዓብዩ ጌታ ምትሀት በጣም ጠንካራ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ስህተቶች በዓለም ላይ ይታያሉ፡፡ ይህም ምንም እንኳን አንዱ ወገን በመንፈሳዊ ስርዓት ክትትሉ በጥብቅ የተሰማራ ቢሆንም እንኳን ነው፡፡ ስለዚህ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ይህንን ነጥብ በትእዛዙ በግልፅ አቅርቦልን ይገኛል፡፡ ይህም በቼታንያ መሀፕራብሁ የቀረበልን ፍልስፍና ነው፡፡ በብሀገቨድ ጊታም የሽሪ ክርሽና የመደምደሚያው ጥቅስ እንዲህ ይላል፡፡ ”ሳርቫ ድሀርማ ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ“ (ብጊ፡ 18.66) በዚህም ጥቅስ የገለፀልን የዓብይነት ደረጃውን ነው፡፡ እርሱም ሽሪ ክርሽና ዓብዩ የመንግስተ ሰማያት ጌታ መሆኑን ነው፡፡ በዚህም ጥቅስ ሽሪ ክርሽና ትእዛዙን ሰጥቶናል፡፡ ”አንተ ተንኮለኛ ሁሉንም ነገር ትተህ ለእኔ ሙሉ ልቦናህን መስጠት ይገባሀል፡፡ በዚህም ደስተኛ ለመሆን ትበቃለህ፡፡“ ይህም የብሀገቨድ ጊታ የመጨረሻው ትእዛዝ ነው፡፡ ቼታንያ መሀፕራብሁ ሽሪ ክርሽና እራሱ ነው፡፡ ቢሆንም ግን በዚህ ምድር የወረደው የሽሪ ክርሽና አገልጋይን ተመስሎ ነው፡፡ ስለዚህ እርሱም ሽሪ ክርሽና የተናገረውን ደግሞ አዞናል፡፡ ”ሙሉ ልቦናህን ስጥ፡፡“ ቼታንያ መሀፕራብሁ እንደገለፀልንም “እያንዳንዱ ሕያው ነዋሪ ነፍሳት የሽሪ ክርሽና አገልጋይ ነው፡፡” ስለዚህ እንደ አገልጋይነቱም ሙሉ ልቦናውን መስጠት ይገባዋል፡፡ የአገልጋይ ሀላፊነትም ሙሉ ልቦናን መስጠት ነው፡፡ ከአለቃው ጋር መከራከር እና “ከአንተ ጋር እኩል ነኝ፡፡” በማለት ማሰብ አይገባውም፡፡ እንደዚህ ማሰብ ግን የአክራሪ ወይንም የእብድ ሀሳብ ነው፡፡ “ፒሻቺ ፓይሌ ዬና ማቲ ቻና ሃያ ማያ ግራስታ ጂቬራ ሴ ዳሳ ኡፓጃያ” አገልጋይ ጌታ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ የማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ዓይነቱ የተሳሳተ አስተሳሰብ ሕይወታችንን እስከመራን ድረስ፤ ይህም “እኔ አገልጋይ አይደለሁም፡፡ እኔ ጌታ ነኝ” የሚል አስተሳሰብ እስካለን ድረስ ከችግር ልንርቅ አንችልም፡፡ በዚህ አስተሳሰብ እስካለን ድረስ ማያ ችግሮችን ስታቀርብ ትገኛለች፡፡ “ዳይቪ ሂ ኢሻ” ይህም ልክ እንደ ሕግ ሰባሪዎች፣ አታላዮች እና በሌብነት እንደተሰማሩ ሰዎች ይቆጠራል፡፡ እንደዚህም ዓይነት ሰዎች በመንግስትን ትእዛዝ ሲቀወሙ ይታያሉ፡፡ “ስለ መንግስት ምንም ግድ አይሰጠኝም።“ ብለውም ይናገራሉ፡፡ ይህም ማለት ደግሞ ይህ ሰው በፍቃዱ ስቃይን ለመቀበል ተዘጋጀ ማለት ነው፡፡ የመንግስትንም ሕግ ምላሽ ሲያገለግል ይገኛል፡፡ ሕግንም በመስበር ተጠንቅቆ የማይኖር ከሆነ ከግዜ በኋላ ወደ እስር ቤት በግባቱ የማይቀር ነው፡፡ ከዚያም በጉልበት፣ በግርፍያ፣ በቅጣት ጥፋቱን እንዲቀበል ይደረጋል፡፡ ”አዎን አጥፍቻለሁ፡፡“

ይህ ማያ ይባላል፡፡ ”ደይቪ ሂ ኤሻ ጉናማዪ ማማ ማያ ዱራትያያ“ (ብጊ፡ 7.14) ሁላችንም በማያ ግዛት ስር እንገኛለን፡፡ ”ፕራክርቴ ክሪያማናኒ ጉናይህ ካርማኒ ሳርቫሻሀ“ (ብጊ፡ 3.27) ለምን? ምክንያቱም ራሳችንን ጌታ አድርገን በማወጃችን ነው፡፡ አገልጋይ ራሱን ጌታ ነኝ ብሎ ያውጃል፡፡ በዚህም ምክንያት ስቃይ ይከተለናል፡፡ ከዚህም በኋላ ”እኔ አገልጋይ እንጂ ጌታ አይደለሁም“ ብለን ስንቀበል፤ የነበረን ስቃይ ሁሉ ይቆማል፡፡ ይህም በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው የፍልስፍና ትምህርት ነው፡፡ ይህም ”ሙክቲ“ ወይንም ነፃነት ይባላል፡፡ ሙክቲ ማለትም ወደ ትክክለኛው ደረጃህ ተመለስ ማለት ነው፡፡ ይህም ሙክቲ ይባላል፡፡ ሙክቲም በሽሪማድ ብሀገቨታም ውስጥ ተገልፆልናል፡፡ ”ሙክቲር ሂትቫ አንያትሀ ሩፓም ስቫሩፔና ቭያቫስትሂቲህ“ (ሽብ፡ 2.10.6) ሙክቲ ማለት ይህንን ስሜት የማይሰጥ አስተሳሰብ ማቆም ማለት ነው፡፡ ”አንያትሀ“ አገልጋይ ሆኖ እኔ ጌታ ነኝ ብሎ ያስባል፡፡ ይህ ”አንያትሀ“ ይባላል፡፡ ይህም ተቃራኒ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን የመሰለውን የተቃረነ አስተሳሰብ ወይንም ጌታ ነኝ የሚለው አስተሳሰቡን እርግፍ አድርጎ ሲተው፤ ወዲያውኑ ወደ ”ሙክቲ“ ደረጃ ወይንም ወደ ነፃነት ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ ሙክቲን ለማግኘት ብዙ ግዜ መውሰድ አያስፈልገንም፡፡ ወይንም ደግሞ በጣም ጥብቅ የሆነ ስርዓትን በመከተል ብዙ ትግል ማድረግ አያስፈልገውም፡፡ ወይንም ደግሞ ወደ ጫካ በመሄድ፣ ወደ ሂማላያ ተራሮች በመሄድ እና በአፍንጫ ላይ በማተኮር ጥልቅ መንፈሳዊ ትግል ማድረግም አያስፈልገውም፡፡ ብዙ ነገሮችን ማድረግ አያስፈልገውም፡፡ የሚያስፈልገውም ይህንን ቀላል ነገር በትክክል መረዳት ብቻ ነው፡፡ ይህም ”እኔ የሽሪ ክርሽና አገልጋይ ነኝ፡፡“ በማለት ነው፡፡ በዚህም ወዲያውኑ ”ሙክታ“ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም የተሰጠውም የሙክቲ ትርጉም ይኅው ነው፡፡ ”ሙክቲር ሂትቫ አንያትሀ ሩፓም ስቫሩፔና አቫስቲሂቲህ“ ይህም ልክ በእስር ቤት እንዳለ ወንጀለኛ ይመሰላል፡፡ ይህም ወንጀለኛ ትሁት ለመሆን ከበቃ እና ”ከአሁን በኋላ ሕግ አክባሪ እሆናለሁ፡፡“ ብሎ ካመነ እና ”ከአሁን በኋላ የመንግስትን ትእዛዝ እና ሕግጋት በጥሞና እከታተላለሁ፡፡“ የሚል ከሆነ መንግስት በዚህ አንደበቱ ምክንያት የእስር ቤቱን ግዜ ሊያሳጥርለት እና ያለ ወቅቱ በግዜ ከእስር ቤቱ ነፃ ሊያደርገው ይችላል፡፡ በዚህም ዓይነት አንደበት ከቁሳዊው ዓለም እስር ቤት ወዲያውኑ ነፃ ለመሆን እንችላለን፡፡ ይህም የሽሪ ቼታንያን ትምህርት የምንከተል ከሆነ ነው፡፡ ”ጂቬራ ስቫሩፕ ሆይ ኒትያ ክርስኔታ ዳስ“ (ቼቻ፡ ማድህያ 20.108-109)