AM/Prabhupada 0107 - የቁሳዊ ገላን እንደገና ለመውሰድ እንዳትበቁ፡፡



Lecture on BG 4.17 -- Bombay, April 6, 1974

ምንም እንኳን የሀብታም ቤተሰብ ገላ ሆነ የድሀ ቤተሰብ ገላ ኖረን ለውጥ የሚያመጣው ነገር አይኖርም፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ የተወለደ ሰው ለሶስቱ ዓይነት መከራዎች መጋለጡ ስለማይቀር ነው፡፡ ለምሳሌ የታይፎይድ በሽታ ሲመጣ ይህ የሀብታም ሰውነት ነው ወይንም ይህ የድሀ ሰውነት ነው ብሎ አይመርጥም፡፡ የታይፎይድ በሽታ ሲመጣ ምንም እንኳን አንዱ የሀብታም ሰውነት ወይንም ሌላው የድሀ ሰውነት ቢኖረውም ሁለቱም ከተመሳሰለ የበሽታ ስቃይ ሊርቁ አይችሉም፡፡ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንኳን እያለን ሁላችን የተመሳሰለ ስቃይ ይደርስብናል፡፡ ይህም ምንም እንኳን ህፃኑ በንግስቲት ማህፀን ውስጥም ሆነ በጫማ ሰሪ ሚስትም ማህፀንም ውስጥ እንኳን ቢሆን ነው፡፡ በዚህም ማህፀን ውስጥ ህፃኑ ታምቆ እና ተዘቅዝቆ ሲኖር ይገኛል፡፡ ይህንንም ስቃይ ብዙ ያልተረዱ አሉ፡፡ "ጃንማ ምርትዩ ጃራ" በምድር ላይ የተለያዩ ስቃዮች አሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ የመወለድ ስርዓቱ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በመወለድ፣ በመሞት፣ በመታመም እና በማርጀት ብዙ የተለያዩ ስቃዮች አሉ፡፡ ሀብታም ሆነን ወይንም ድሀ ሆንን እንድሜያችን ሲገፋ ሁላችንም በአካል የአቅም ጉድለት ስንሰቃይ እንገኛለን፡፡ እንደዚህም ሁሉ በቬዳዎች እንዲህ ብሎ ተጠቅሷል፡፡ "ጃንማ ምርቱዩ ጃራ ቭያድሂ (BG 13.9) "ጃራ" እንዲሁም "ቭያዲ እና ምርትዩ" ፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ሰብዓዊ ገላችን ምን ዓይነት ስቃይ የተሞላበት ደረጃ ላይ እንዳለ በትክክል የተረዳንበት ደረጃ ላይ አይደለንም፡፡ "ሻስትራ" ወይንም የቬዲክ ቅዱስ መፃህፍት እንዲህ ይሉናል፡፡ "ይህንን ቁሳዊ ገላ እንደገና ተወልደህ እንዳትይዝ፡፡" "ና ሳድሁ ማንዬ" "በተደጋጋሚ እየተወለድክ ይህንን ቁሳዊ ገላ ለመያዝ በቅተሀል፡፡ ይህ ጥሩ አይደለም፡፡" "ና ሳድሁ ማንዬ ያታ አትማናሀ" አትማናሀ ወይንም ነፍስ በዚህ በሰብአዊ ቁሳዊ ገላ ውስጥ ተጠምዳ ትገኛለች፡፡ "ያታ አትማኖ ያም አሳን አፒ" ምንም እንኳን ጊዜያዊ ቢሆንም ይህንን ገላ አግኝቼአለሁ፡፡ "ክሌሻ አሳ ዴሀሀ" ሰለዚህ በዚህ ስቃይ በተሞላበት ቁሳዊ ገላ በተደጋጋሚ እንዳንጠመድበት ከተፈለገ ስለ "ካርማ" እና ሰለ "ቪካርማ" በትክክል መረዳት ይገባናል፡፡ የክርሽናም ምክር ይኅው ነው፡፡ "ካርማኖ ሁ አፒ ቦድሀቭያም ቦድሀቭያም ቻ ቪካርማናሀ አካርማናስ ቻ ቦድሃቭያም" "አካርማና" ማለት ምንም ተመላሽ ውጤት የሌለው ማለት ነው፡፡ "ካርማ" ማለት ደግሞ ተመላሽ ውጤት ያለው ማለት ነው፡፡ ጥሩ ነገር የምናደርግ ከሆነ በተፈጥሮ ጥሩ ነገር በምላሹ ይመጣልናል፡፡ እነዚህም ጥሩ ነገሮች ቆንጆ ገላ፣ ጥሩ ትምህርት፣ ጥሩ ቤተሰብ እና ሀብትን የመሳሰሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ደስ የሚሰኙ ናቸው፡፡ ወደ ገነትም ለመሄድ የምንመኘው እንዲህ ዓይነት ጥሩ ነገሮች ሰለሚገኙ ነው፡፡ ነገር ግን ሰው ያልተረዳው ነገር ቢኖር ምንም እንኳን ወደ ገነት ብንሄድም እንኳን እነዚሁ "ጃንማ፣ ምርትዩ፣ ጃራ፣ ብያድሂ" ተብለው የሚታወቁት ስቃዮች አይጠፉም፡፡ ስለዚህም ሽሪ ክርሽና ወደ እነዚህ የገነት ፕላኔቶች በመሄድ የገነት ገላ እንድንይዝ አይመክረንም፡፡ በብሀገቨድ ጊታ እንደገለፀውም "አ ብራህማ ብሁቫና ሎካ ፑናር አቫርቲኖ አርጁና" (BG 8.16) ምንም እንኳን "ብራህማ ሎካ" ወደ ተባለው ወደ ከፍተኛው የገነት ፕላኔት ብንሄድም እንኳን ተደጋጋሚው ትውልድ እና ሞት አይለየንም፡፡ "ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም ማማ" (BG 15.6) "ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ" የዘነጋነው ነገር ቢኖር ግን መንፈሳዊ ዓለም ወይንም "ድሀም" መኖሩን ነው፡፡ እንደ ምንም ብለን ወደዚህ መንፈሳዊ ዓለም ወይም "ድሀም" ብንዘዋወር ግን ውጤቱ "ና ኒቫርታንቴ ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም ማማ" ይሆናል፡፡ በሌላም ቦታ እንዲህ ብሎ ተጠቅሷል "ትያክትቫ ዴሀም ፑናር ጃንማ ናይቲ ማም ኢቲ" (BG 4.9) ሽሪ ክርሽና ዓብዩ የመንግስተ ሰማያት ጌታ እንደሆነ ብዙ ያልተረዱ ሰዎች አሉ፡፡ እርሱም የእራሱ መንፈሳዊ ቦታ አለው፡፡ ማናችንም ብንሆን ወደ እዚህ መንፈሳዊ ዓለም ለመሄድ እንችላለን፡፡ ታድያ እንዴት አድረገን ነው ለመሄድ የምንችለው? "ያንቲ ዴቫ ቭርታ ዴቫን ፒትርን ያንቲ ፒትር ቭራታሀ ብሁታኒ ያንቲ ብሁቴጅያ ያንቲ ማድ ያጂኖ ፒ ማም" (BG 9.25) "አንድ ሰው ወደ እኔ በፍቅር አገልግሎት መንፈስ የቀረበ ከሆነ፣ ስግደት የሚያደርግልኝ ከሆነ ወይንም በብሀክቲ ዮጋ የተመሰጠ ከሆነ ወደ እኔ መምጣቱ የተረጋገጠ ነው፡፡" በሌላም ወገን እንዲህ ብሎ ጠቅሶልናል፡፡ "ብሀትያ ማም አብሂጃናቲ ያቫን ያሽ ቻስሚ" (BG 18.55) ስለዚህ ዋናው ስራችን ክርሽናን በትክክል መረዳት መሆን አለበት፡፡ “ያግናርትሄ ካርማ” ይህም አካርማ ይባላል፡፡ ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ “አካርማና አፒ ቦድሀቭያም አካርማናስ ቻ ቦድሃቭያም” “አካርማ” ማለት ምላሽ የሌለው ማለት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ውስጥ ለስሜታዊ ደስታ የምንቀሳቀስ ከሆነ ምላሽ ውጤት የሚያመጣ ይሆኖል፡፡ ለምሳሌ አንድ ወታደር በጦር ሜዳ ላይ ጠላት ቢገድል የወርቅ ሜዳል ሊሸለም ይችላል፡፡ ይኅው ወታደር ግን ቤቱ ሲሄድ ለግል ጥቅሙ ወይንም ስሜቱን ለማርካት ሰው ቢገድል እስከመሰቀል ሊደርስ ይችላል፡፡ ለምን? በፍርድ ቤትም ሂዶ “ጌታዬ ሆይ በጦር ሜዳ ላይ እያለሁ እኮ ብዙ ሰዎች በመግደሌ የወርቅ ሜዳል ተሸልሜአለሁ፡፡” ታድያ አሁን አንድ ሰው በመግደሌ ለምን ትሰቅሉኛላችሁ? “ምክንያቱም ሰው የገደልከው የግል ጥቅምህን ለማግኘት ወይንም የግል ስሜትህን ለማርካት በመሆኑ ነው፡፡” በጦር ሜዳ ግን የሰራኅው ሁሉ በመንግስት የተደገፈ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም እንቅስቃሴ ወይንም “ካርማ” ለክርሽና ደስታ የተደረገ ከሆነ “አካርማ” ይባላል፡፡ ምክንያቱም ምላሽ መከራን የማይስከትል በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ለግል ጥቅማችን እና የግል ስሜታችንን ለማርካት የምናደርገው ነገር በሙሉ በምላሹ መከራን የሚያስከትል ይሆናል፡፡ ይህም ጥሩ ወይንም መጥፎ ውጤት እንደስራችን እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ክርሽና እንደዚህ ብሎናል፡፡ “ካርማኖ ሂ ቦድሃቭያም ቦድሀቫያም ቻ ቪካርማናሀ” “አካርማናሽ ቻ ቦድሃቭያም ጋሀና ካርማኖ ግቲህ” ምን ዓይነት ስራ ላይ መሰማራት እንደሚገባን ለማወቅ በጣም አዳጋች ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ መመሪያ መውሰድ የሚገባን ከሽሪ ክርሽና ነው፡፡ ወይንም ከሻስትራ የቬዲክ ቅዱስ መፃህፍት እና ከጉሩ ወይንም መንፈሳዊ መምህር መሆን አለበት፡፡ በዚህም መንገድ ሕይወታችን የተሳካ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ሀሬ ክርሽና፡፡