AM/Prabhupada 0117 - የነፃ ሆቴል እና የነፃ የመተኛ ክፍሎች፡፡



Lecture on SB 7.9.24 -- Mayapur, March 2, 1976

ትክክለኛ አንደበት የሚኖረን አንደበታችን በዓብዩ ጌታ አገልግሎት የተመሰጠ ሲሆን ነው፡፡ ይህም የሰው ልጅ ትክክለኛው የስልጣኔ ምልክት ነው፡፡ እያንዳንዱም ሴት ልጅ የባለቤትዋ ትሁት አገልጋይ መሆን ይጠበቅባታል፡፡ እያንዳንዱም ሰው የሽሪ ክርሽና መቶ በመቶ አገልጋይ መሆን ይገባዋል፡፡ የህንድም ስልጣኔ በዚሁ የተመሰረተ ነው፡፡ በትዳር ላይ ያሉም ባል እና ሚስት በእኩልነት ደረጃ የተመሰጠ አንደበት አይታይባቸውም። በአሜሪካ እና በአውሮፓ ውስጥ ይህ የእኩልነት ትግል ሲካሄድ ይታያል፡፡ ይህም የቬዲክ ስልጣኔ አይደለም፡፡ የቬዲክ ስልጣኔ የሚያስተምረው ባልየው የዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ትሁት እና ትጉህ አገልጋይ እንዲሆን ነው፡፡ ሚስቱም ለባለቤትዋ ትሁት አገልጋይ እንድትሆን ይጠበቅባታል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጥቅስ እንደተገለፀው "ኡፓናያ ማም ኒጃ ብህርትያ ፓርሽቫም" ሽብ፡ 7 9 24 ይህም ትክክለኛ አቀራረብ ነው፡፡ ባህታዊው ናራዳ ሙኒ እንዴት ወንዶች እና ሴቶች በስነ ስርዓት መኖር እንደሚገባቸው ገልጿል፡፡ እነዚህንም ነጥቦች ስንወያይ የነበረ ግዜ በቴፕ ቀድተነዋል፡፡ ከዚህም ቅጂ ውይይቱን ማዳመጥ ትችላላችሁ፡፡ በዚህም ውይይት የሁሉም ጌታ ልንሆን እንደማንችል ተገልጿል፡፡ የሁሉም ጌታ ለመሆን ጥረት ማድረግ ዋጋ የሌለው ነው፡፡ ምክንያቱም ሊሆን የማይችል ነገር በመሆኑ ነው፡፡ "አሀንካራ ቪሙድሀትማ ካርታሃም ኢቲ ማንያቴ (ብጊ፡ 3 27) የሁሉም ጌታ ለመሆን አይቻልም፡፡ "ጂቬራ ስቫሩፕ ሆይ ኒትያ ክርሽና ዳስ" (ቼቻ ማድህያ 20 108-109) ወንድም ሆነ ሴት ሁሉም የሽሪ ክርሽና አገልጋዮች ናቸው፡፡ ይህንንም መንፈስ በመከተል ልምምድ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህም እንዴት አድርገን የዓብዩ ጌታ ትሁት አገልጋይ መሆን እንደምንችል በመማር ነው፡፡ ይህም በቀጥታ የአብዩ ጌታ አገልጋይ ብቻ መሆን ሳይሆን የእርሱ አገልጋዮችም አገልጋይ መሆን ይገባናል፡፡ ይህም የፓራምፓራ ወይንም የድቁና አገልጋይ ይባላል፡፡ የእኔ መንፈሳዊ አባት የመንፈሳዊ አባቱ አገልጋይ ነው፡፡ እኔም እንደዚሁ የመንፈሳዊ አባቴ አገልጋይ ነኝ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማሰብ የሚኖርብን "እኔ የአገልጋዮች አገልጋnይ ነኝ" በማለት ነው፡፡ ጌታ ለመሆን ምንም ጥያቄ አያስፈልግም፡፡ ጌታ ለመሆን ማሰብ የዓለማዊ ኑሮ በሽታ ነው፡፡ (ቼቻ ማድህያ፡ 13 80) "ክርሽና ቡሁሊያ ጂቫ ብሆጋ ቫንቻ ካሬ ፓሳቴ ማያ ታሬ ጃፓቲያ ድሀሬ" በሀብት ልባችን ማበጥ ሲጀምር "አሁን ጌታ ለመሆን እየበቃሁ ነው" በማለት እናስባለን፡፡ "ከአሁን በኋላ ትእዛዝ መስጠት ብቻ ነው፡፡ ማንንም ሰው መከተል አያስፈልገኝም፡፡" ብለን ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ይህም "ማያ" ወይንም ከእውነት የራቀ ይባላል፡፡ ይህም ዓይነቱ የዓለማዊ ኑሮ በሽታ ቀድሞ በሕዋ ውስጥ ከተፈጠረው ጌታ ብራህማ ጀምሮ እስከ ጉንዳኑ ድረስ ያለ በሽታ ነው፡፡ መንፈሳዊው ፕራህላድ ማሀራጅ ጌታ ለመሆን መጣር ለሀሰተኛ ማእረግ እንደሚያጋልጥ በትክክል በመረዳት ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ እንዲህም በማለት አስተምሯል፡፡ "ይህን የሀሰት ማእረግ ተረድቼዋለሁ፡፡ ስለዚህ በመንፈሳዊ አገልግሎት እንድሰማራ አድርጉኝ፡፡" "ኒጃ ብህርትያ ፓርሻቫም" ይህም ማለት ልክ ለልምምድ እንደመጣ አዲስ ባለሙያተኛ ነው፡፡ ይህም ለማጅ አዲስ ባለሙያተኛ ወደ ሙያተኛው በመሄድ ለመልመድ ይበቃል፡፡ ከጥቂት ግዜ በኋላም ልምምዱን በመውሰድ ብዙ ነገር ለመማር ይችላል፡፡ ስለዚህ ፕራህላድ እንዲህ ብሏል፡፡ "ኒጃ ብህርትያ ፓርሻቫም" "ወዲያዉኑ አዋቂ እና ትሁት አገልጋይ ለመሆን ባልበቃም እድሉን ከሰጣችሁኝ ቀስ በቀስ ለመሆን እችላለሁ፡፡" የእኛም ድርጅት ይህንን በመሰለ ዓላማ የተመረኮዘ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ ድርጅታችን በመምጣት የነፃ ሆቴል እና መኖርያ እንዳገኘ ሰው ለመኖር ያቅድ ይሆናል፡፡ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ግን ሕይወቱን ስኬታማ አያደርገውም፡፡ እንዴት አድርጎ ለማገልገል ግን መማር ይኖርበታል፡፡ "ኒጃ ብህርትያ ፓርሻቫም" ከሌሎች አገልጋዮችም መማር ይኖርበታል፡፡ እንዴት አድርገው ለሀያ አራት ሰዓት እንደሚያገለግሉ በማየት መማር ይኖርበታል፡፡ በዚህም መንገድ ወደ ድርጅቱ መምጣቱ ስኬታማ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ የነፃ ሆቴል ነው በማለት ለግል ጥቅም የቆመ ከሆነ ግን ሕይወቱን ስኬታማ ለማድረግ አይችልም፡፡ የነፃ መኖርያ ብሎ በመምጣት እና በነፃ ስሜትን ለማርካት በመምጣት መላ ድርጅቱ ሊበላሽ ይችላል፡፡ መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ እያንዳንዱ የጂቢሲ አባላት ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በድርጅቱ ውስጥ እንዳይሰፍን ወይንም እንዳይጨምር ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ሰው በድርጅቱ ውስጥ በመሆን ለማገልገል ከፍተኛ ፍላጎት እንዲኖረው ያስፈልገዋል፡፡ እንዴት አድርጎ ለማገልገልም መማር ያስፈልገዋል፡፡ "ኒጃ ብህርትያ ፓርሽቫም" በዚህም ዓይነት መንገድ ሕይወታችን ስኬታማ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡