AM/Prabhupada 0119 - መንፈሳዊው ነፍስ ሁሌ እንደ አረንጓዴ ነው፡፡



Lecture on BG 2.1-10 and Talk -- Los Angeles, November 25, 1968

ፕራብሁፓድ:አዎን:

ሽሪማቲ:እድሜ ማለት እርሱ ይሆን?ነፍስ ከገላ ስትወጣ ይህስ እርጅና ማለት ነውን?

ፕራብሁፓድ:አይደለም:ነፍስ አረጀች ማለት አይደለም:ገላችን እየተቀያየረ ነው:ያ ነው ሂደቱ: ይህም ተገልጿል: “ዴሂኖ ስሚን ያትሃ ዴሄ:ኮማራም ዮቫናም ጃራ:ታትሃ ደሃንታራ ፕራፕቲር ድሂራስ ታትራ ና ሙህያቲ” (ብጊ 2 13) ነፍስ ሁልግዜ ለዘለአለም የማታረጅ ለምለም ናት:ገላ ግን ሁልግዜ ይቀያየራል: ይህን መገንዘብ አለባችሁ:ገላ ሁልግዜ እንደተቀያየረ ነው:ይህን ሁሉም ይረዳል: በልጅነታችሁ እንደምታውቁት ገላችሁ ልዩ ነበር: ልክ እንደ እዚች ህጻን:የተለየ ገላ ነበር: ይህች ህጻን ደግሞ:ወጣት ልጅአገረድ ስትሆን የተለየ ገላ ትይዛለች: ነገር ግን:ነፍስ በዚህኛውም ሆነ በዚያኛውም ገላ ነበረች: ይህ ነው ማስረጃው:ነፍስ አትቀያየርም:ነገር ግን ገላችን ሁሌ እንደተቀያየረ ነው: ይህ ነው መረጃው:እኔ ስለ ልጅነቴ አስብ ይሆናል: ይህም ማለት ያ ስለልጅነት የማስበው ገላ:የእኔው የእራሴ ገላ ነበር: በልጅነቴ የማደርገውን ነገር ሁሉ አስታውሳለሁ:ይህንንም ያንንም ሳደርግ: ነገር ግን ያ የልጅነት ገላ ሂዷል: ይህም ማለት የልጅነት ገላዬ ተቀይሯል: እኔ ግን እስከ አሁን አለሁ አልተቀየርኩም:ይህ ነው መደምደሚያው: ይህ አይደለምን? ይህ ቀላል እውነት ነው: ገላው በተቀየረ ግዜ ሁሉ እኔ አልቀየርም: ሌላ ገላ ውስጥም እገባ ይሆናል:ይህ እኔን ሊለውጠኝም አይችልም: “ታትሃ ዴሃንታራ ፕራፕቲር ድሂራስ ታትራ ና ሙህያቲ” (ብጊ 2 13) ልክ ገላዬን አሁን እንደምቀያይረው ሁሉ: እንደዚሁም ሁሉ በመጨረሻ በሞት ግዜም ሲቀየር:እኔ ሞትኩኝ ማለት አይደለም: ሌላ ገላ ውስጥ እገባለሁ እንጂ:ይህም ተገልጿል:“ቫሳምሲ ጂርናኒ ያትሃ (ብጊ 2 22) ለምሳሌ ሳንያሲ (ባህታዊ)ከመሆኔ በፊት:እንደ ጀንትል ሰው ልብስ እለብስ ነበረ: አሁን ግን ልብሴ የተለየ ነው:ይህም ማለት ሞትኩኝ ማለት አይደለም: አይደለም:ገላዬን መቀየር:ልብሴን እንደቀየርኩት ማለት ነው: