AM/Prabhupada 0182 - እራሳችሁን ከሀጥያት የነፃ ደረጃ ላይ አስፍሩት፡፡



Lecture on SB 2.3.15 -- Los Angeles, June 1, 1972

አንድ ጥቅም ያለው ምንድነው ሰለ ክርሽና በመስማት ብቻ አንድ ሰው ከሀጥያት ንፁህ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም በማዳማጥ ብቻ ነው፡፡ ሀጥያተኞች ካልሆንን በስተቀረ ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም አንመጣም፡፡ ወደ መንፈሳዊ ዓለም ከመሄዳችንም በፊት ከኃጥያት ሁሉ ነፃ መሆን ይገባናል፡፡ ምክንያቱም የአብዩ የመላእክት ጌታ ንጹህ ሰለሆነ እና ቤተ መንግስቱም ንጹህ ሰለሆነ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ንፁህ አንደበት የሌለው ለመግባት አይችልም፡፡ ሰለዚህ አንድ ሰው ንፁህ መሆን አለበት፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ተገልፆልናል፡፡ “ዬሻም አንታ ጋታም ፓፓም” “ከሀጥያት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ ብቻ” “ዬሻም ትቭ አንታ ጋታም ፓፓም ጃናናም ፑንያ ካርማናም” “እንዲሁም ሁልግዜ በረከት በተሞላበት ስራዎች ላይ የተሰማራ እና ምንም ዓይነት ሀጥያታዊ ስራ ውስጥ ያልተሰማራ” ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር ዓላማው ይህንን እድል ለመስጠት እና ሀጥያችን ሁሉ እንዲሰረዝ ለማድረግ ነው፡፡ እራሱንም ከእነዚህ አላግባብ ነገሮች እንዲተበቅ ማድረግ፡፡ ያለአግባብ ወሲብ አልኮል መጠጣት እና መስከር ስጋ መብላት እና ቁማር መጫወት፡፡ እነዝህንም መመሪያዎች ብንከተላቸው ድቁና ከወሰድን በኃላ ሁሉ ሀጥያታችን ሊታጠቡልን ይችላል፡፡ ከዚያም በዚሁ በንፁህ ደረጃ የምቀጥል ከሆነ እንዴት አድርጌ ወደ ሀጥያት እንደገና ለመውደቅ እበቃለሁ? ነገር ግን አንዴ ሀጥያታችንን ካጠብን በኋላ ወይም ገላ ታጥበን እንደ ገና ወደ አቧራው የምንከባለል ከሆነ የመታጠብጥቅሙ ምንድን ነው? ይህ ስርዓት አይሰራም፡፡ እንዲህ የምትል ከሆነ “አሁን እታጠብ እና እንደገና ወደ አቧራ እሄዳለሁ” የምትል ከሆነ የመታጠብህ ጥቅሙ ምንድን ነው? በመጀመሪያ መታጠብ፡፡ ከታጠቡም በኋላ ንጽህናን መጠበቅ፡፡ ይህ ነው የሚጠበቅብን፡፡ በመንፈሳዊ ደረጃ ይህም የሚቻለው ሁልግዜ እራሳችንን ከክርሽና ጋር ያለንን ግኑኝነት የምናጠባክር ከሆነ ነው፡፡ ይህም ሰለእርሱ በማዳመጥ ነው፡፡ በዚህ መንገድ መንፈሳዊ ንፅህናችንን መጠበቅ አለብን፡፡ ይህም “ፑንያ ሽራቫና ኪርታናሀ” ይባላል፡፡ ሰለ ክርሽና የምትሰም ከሆነ ሁልግዜ በረከት የሞላባችሁ ትሆናላችሁ፡፡ “ፑንያ” “ፑንያ ስራቫና ክርታናሀ” ወይ ዘምሩ ወይንም...... ሰለዚህ የእኛ ምክር ሁልግዜ እንድትዘምሩ ነው፡፡ “ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሀሬ ሀሬ ሀሬ ራማ ሀሬ ራማ ራማ ራማ ሀሬ ሀሬ” ሰለዚህ ወደ ታች ወደ ሀጥያታዊ ደረጃ እንዳንወድቅ ሁልግዜ መጠንቀቅ ይገባናል ሁሉም ሰው መጠንቀቅ ይገባዋል፡፡ ሁል ግዜ መዘመር ያሰፈልገባል፡፡ በዚህ ስርዓት ሁሉም ነገር ደህና ይሆናል። “ሽርንቫታም ስቫ ካታህ ክርሽና ፑንያ ሳርቫና ኪርታናህ” (ሽብ፡1 2 17) ቀስ በቀስ ሰለ ክርሽና ሁሌ መስማት ስንጀምር በልባችን ውስጥ ያለው ቆሻሻ ሁሉ እየፀዳ ይመጣል፡፡ እነዚህም ቆሻሻ ነገሮች ማለት “ይህ ገላ እኔ ነኝ“ ብሎ ማሰብ “እኔ አሜሪካዊ ነኝ እኔ ህንድ ነኝ እኔ እስላም ነኝ እኔ ይህ ነኝ እኔ ያኝ” ብሎ ማሰብን ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የውስጣዊ ነፍስ ሁሉ ክዳኖች ናቸው፡፡ በቁሳዊ ገላ ያልተሸፈነው ነፍስ ሙሉ በሙሉ ንቃት ያለው ነው፡፡ “እኔ የዘለዓለማዊ የአብዩ ጌታ አገልጋይ ነኝ” ብሎም የነቃ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ ነፍስ ምንም ማነነት የለውም፡፡ ይህም ነፃ የሆነ ደረጃ ወይንም “ሙክቲ” ይባላል፡፡ አንድ ሰው ይህ ዓይነቱ ንቃት ሲኖረው “እኔ የአቡዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽና የዘለዓለም ትሁት አገልጋይ ነኝ” “ስራዬም ሁሉ እርሱን ማገልገል ነው” ብሎ የተገነዘበ ሁሉ ነፃነት ወይንም “ሙክቲ” ያለው ነው፡፡ ሙክቲ ማለት ሁለት እግር እና ሁለት እጅ ይኖርሀል ማለት አይደለም፡፡ ሁሉም እንደ አለ ሆኖ ንፁህ የሆነ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በጉንፋን እየተሰቃየ ነው እንበል፡፡ ለዚህም ብዙ ምልክቶች ይኖሩታል። ነገር ግን ከዚህ በሽታ ሲድን ምልክቶቹ ሁሉ ይጠፋሉ ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለን የነፍሳችን ጉንፋንም ይህ የቁሳዊ ስሜታዊ ደስታ ማሳደድ ነው፡፡ ቁሳዊ ስሜታዊ ደስታ፡፡ ይህ ነው በሽታችን፡፡ ታድያ በዚህ በክርሽና ንቃታችን ተሰማርተን ስንዳብር ይኀው በሽታችን በቁሳዊ ስሜት ለመደሰት ያለን ፍላጎት ይቆማል፡፡ ይህ ነው ልዩ ነቱ፡፡ እንዴት በክርሽና ንቃታችንም እንደዳበርን ለማወቅ የምንችለው የቁሳዊ ዓለም ሴሜታችንን ለማርካት ያለን ፍላጎት ሲቀንስ ነው፡፡