AM/Prabhupada 0202 - ከመንፈሳዊ ሰባኪ በላይ ማን ፍቅርን ለመስጠት ይችላል



Morning Walk -- May 17, 1975, Perth

አሞግሀ፡ ሰጎኖች ጭንቅላታቸውን በመሬት ውስጥ ይቀብራሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ፓራማሀምሳ፡ ብዙዎች ወደ ሀሬ ክርሽና እንቅስቃሴ በመግባት ላይ ሰለሚታዩ ብዙ እርምጃ እንደ አለ ግልፅ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ እነርሱም ብዙ እርምጃ ወደፊት እየወሰዱ ነው፡፡ “ብሀቫ መሀ ድቫግኒ ኒርቫፓናም” በዚህም እንቅስቃሴ ውስጥ የቁሳዊ ዓለም ጭነቀቶች ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ እነርሱም ወደፊት ብዙ እርምጃ እያደረጉ ነው፡፡ “ቼቶ ዳርፓናም ማርጃናም ብሀቫ መሀ ዳቫግኒ ኒርቫፓናም (ቼቻ አንትያ፡ 20 12) የሀሬ ክርሽናንም ቅዱስ ስም በመዘመር ይህ የቆሸሸው ልባችን ይፀዳል፡፡ ከፀዳም በኋላ የቁሳዊው ዓለም ችግሮች ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ ጭንቀቶች ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ ፓራማሀምሳ፡ ደስተኞች ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን የክርሽና አገልጋዮች ደስተኞች ይሁኑ እንጂ ብዙ የተግባራዊ ስራ የሚሰሩ አይመስሉም፡፡ ሁሌ ሊዘምሩ እና ሲደንሱ ይታያሉ እንዲሁም ገንዘብ ሲሰበስቡ ይታያሉ፡፡ ነገር ግን ተግባራዊ ስራ ይሚሰሩ አይመስሉም፡፡ እኛ ብዙ ተግባራዊ ስራ እየሰራን እንገኛለን፡፡

ፕራብሁፓድ፡ መደነስ ስራ አይደለምን? መፅሀፍ መፃፍስ ስራ አይደለምን? መጽሀፍ መሸጥስ ስራ አይደለምን? ስራ ማለት ምን ማለት ነው? ህም.... ልክ እንደ ዝንጀሮ መዝለል አለብን? ይህ ስራ ነው? አሞግሀ፡ ነገር ግን እኛ በየሆስፒታሉ እና በአልኮል የተቸገሩትን ሁሉ በመርዳት ላይ እንገኛለን፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም እንዴት አድርገህ ነው የምትረዳቸው፡፡ አንድ ሰው ወደ ሆስፒታል በመሄዱ የማይኖት ይመስልሀል? እንዴትስ አድረገህ ነው የምትረዳቸው? አንተ የምታሰብው ከሆነ አንተ እንደምትረዳቸው ነው፡፡ አሞግሀ፡ ቢሆንም ህይወቱን ሊራዝም ይችላል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይህ ሌላኛው ሞኝነት ነው፡፡ ምን ያህል ግዜ ለመኖር ትችላለህ? የሞት ግዜህ ሲመጣ ለጥቂት ግዜ እንኳን እድሜህን ለማራዘም አትችልም፡፡ የአንድ ሰው የሞቱ ግዜ ሲደርስ ሕይወቱ አከተመች ማለት ነው፡፡ ያንተ መርፌ እና መድሀኒት የአንድ ደቂቃ እንኳን ህይወር የሚሰጥ ይመስልሀል? ሕይወትንስ የሚያራዝም መድሀኒት ያለ ይመስልሀል? አሞግሀ፡ አዎን ያለ ይመስላል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አይኖርም አሞግሀ፡ አንዳንድ ግዜ መድሀኒት ሲሰጥ ሰዎች እድሜያቸው ይራዘማል፡፡ ፓራማሀምሳ፡ እንደሚሉትም የልብ ኦፕራስዮን በማድረግም ሰዎች እድሜያቸው እዲገፋ ለማድረግ ተችሏል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ እንደዚያ ሊሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እኛ ተንኮለኞች እንላቸዋለን፡፡ ለምንስ የእነሱን ቃል እንሰማለን? ልክ እንደ ተንኮለኞች ብቻ ነው ማየት ያለብን፡፡ ይኅው ነው፡፡ (አንድ ሰው ከኋላ እየጮኅ ይገኛል፡፡ ፕራብሁፓድም እየጮኅበት ነው) (ሳቅ) ሌላ ተንኮለኛ ሕይወቱን እየተደሰተ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መላ ዓለም ተንኮለኞች የሞሉበት ነው፡፡ ሰለ እዚህ ዓለም የተቃረነ አስተያየት እንዲኖረን ያሰፈልገናል፡፡ ሰለሁሉም በተቀባይነት ማየት አያስፈልገንም፡፡ ተቃራኒ አስተያየት ከሌለን ወደ አብዩ አምላክ መንፈሳዊ ቤተ መንግስት ለመሄድ ያዳግተናል፡፡ ለዚህ ቁሳዊ ዓለም ትንሽም እንኳን የተሳባችቡ ከሆነ “ይህ ቆንጆ ነው” ወደ እዚሁ ቁሳዊ ዓለም መቅረታችሁ የማይቀር ነው፡፡ አዎን ክርሽና በጣም ኮስታራ ነው፡፡ ፓራማሀምሳ፡ ኢየሱስ “ወንድሞቻችሁን እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት“ ብሎናል። ሰለዚህ ወንድሞቻችንን እንደ እራሳችን የምንወድ ከሆነ....

ፕራብሁፓድ፡ በእርግጥም እንወዳቸዋለን፡፡ የክርሽና ንቃትም እየሰጠናቸው እንገኛለን፡፡ ይህም መውደድ እና በትክክሉ መውደድ ነው፡፡ የምንሰጣቸውም ዘለዓለማዊ ሕይወት ነው እንዲሁም ዘለዓለማዊ ደስታ፡፡ የማንወዳቸው ከሆነ ለምን ይህንን ያህል ልፋት ወስጥ እንገባለን? ሰባኪ የሚያሰተምራቸውን መውደድ አለበት፡፡ አለመለዛ ግን ለምን ይቸገራል? ለእራሱ በቤቱ ማድረግ ይችላል፡፡ለምንስ ብዙ ድካም ውስጥ ይገባል? የማልወድስ ከሆነ ለምንስ በሰማንያ ዓመቴ ወደ እዚህ ለመምጣት ተገደድኩ? ከሰባኪ በላይ ማንስ ሌላ ፍቅር ያለው ይገኛል? እርሱ እንስሶችንም እንኳን ይወዳል? ሰለዚህም “ስጋ አትብሉ” እያለ ሲሰብክ ይገኛል፡፡ እነዚህ ተንኮለኞች እንስሶችን ይወዳሉን? ይበሏቸዋል አገራቸውንም ይወዳሉ ይኅው ነው፡፡ ማንም ሰው የሚወድ የለም፡፡ የስሜታዊ ደስታ ብቻ ነው የሚገኘው፡፡ የሚወድ ሰው ቢኖር ግን በክርሽና ንቃት የዳበረ ነው፡፡ ሌሎች ሁሉ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ሁሉም በስሜታዊ ደስታ ፍላጎት የተመሩ ናቸው፡፡ ከዚያም “ሁሉን እወዳለሁ” የሚል ማስታወቂያ ይለጥፋሉ፡፡ ይኀው ነው ስራቸው፡፡ ሞኞችም ይህን ተቀብለውታል፡፡ “ኦህ ይህ ሰው የበጎ አድራጎት ሰው ነው፡፡” የሚወደውም ሰው የለም፡፡ የሚወደውም ስሜቶቹን ብቻ ነው፡፡ ይኀው ነው፡፡ የሴሜቶቻችን አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡