AM/Prabhupada 0211 - እቅዳችን ሁሉ እንዴት የሽር ቼታንያን ምኞት ለሟሟላት እንደምንችል መሆነ ይኖርበታል፡



Lecture on CC Adi-lila 1.4 -- Mayapur, March 28, 1975

የሽሪ ቼይታንያ መሀብራብሁን በረከት ሳታገኙ በቀጥታ ወደ ክርሽና ንቃት ዘሎ ለመግባት አይቻልም፡፡ በሽሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁ በረከት ማለፍ ደግሞ የሚቻለው ከስድስቱ ጎስዋሚ አገልጋዮች በረከት ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ይህም የፓራምፓራ ስርአት ይባላል፡፡ ሰለዚህም ናሮታማ ዳስ እንዲህ ብሏል፡፡ ”ኤ ቻይ ጎሳይ ጃር ታር ሙይ ዳስ“ ”ታ ሳባራ ፓዳ ሬኑ ሞራ ፓንቻ ግራስ“ ይህም የፓራምፓራ ስርአት ይባላል፡፡ ይህንን ስረአት ዘልሎ ማለፍ አይቻልም፡፡ አንድ ሰው የፓራም ፓራውን ስርዓት ተከትሎ ማለፍ ይገባዋል፡፡ ጎስዋሚዎቹንም ለመቅረብ የሚቻለው በመጀመሪያ መንፈሳዊ አባታችሁን በመቅረብ ነው፡፡ ከዚይም በጎስዋሚዎቹ አማካኝነት ሺሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁን ለመቅረብ ትችላላችሁ፡፡ ሽሪ ክርሽና ቼይታንያንም በመቅረብ ክርሽናን ለመቅረብ ትችላላችሁ፡፡ ይህ ነው ስርዓቱ፡፡ ሰለዚህ ናሮታማ ዳስ ታኩር እንዲህ አለ፡፡ ”ኤቻዬ ጎሳዬ ጃር ታር ሙይ ዳስ“ እኛ የአገልጋዮች ሁሉ አገልጋዮች ነን፡፡ ይህም የቼይታንያ መሀ ብራብሁ ትእዛዝ ነው፡፡ ”ጎፒ ብሀርቱ ፓዳ ካማላዮር ዳሳ ዳሳኑዳሳሀ“ (ቼቻ 13 80) የአገልጋዮች ሁሉ አገልጋይ በሆናችሁ ቁጥር ፍጹም ደረጃ ላይ ለመድረስ ብቁ ትሆናላችሁ፡፡ ነገር ግን በድንገት ጌታ ለመሆን ጥረት የምታደርጉ ከሆነ ግን ወደ ሲኦል ትሄዳላችሁ፡፡ ይኅው ነው፡፡ ይህንንም አታድርጉ፡፡ ይህ ነው የሽሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ትምህርት፡፡ ከአገልጋዮች ሁሉ ስር በመሆን ለማገልገል ይምትጥሩ ከሆነ ወደ ፊት የተራመዳችሁ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ ነገር ግን የሁሉም ጌታ ነኝ ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ወደ ሲኦል ትሄዳላችሁ፡፡ ይህን ነው ስርዓቱ፡፡ ”ዳሳ ዳሳኑዳሳሀ“ ቼታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎ አስተምሮናል፡፡ ሰለዚህ የአገልጋዮች አገልጋይ መቶ ግዜ ወደ ታች በመሄድ አንድ ሰው በክርሽና ንቃቱ ለመበልፀግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ጌታ ለመሆን የሚፈልገው ሁሉ ወደ ሲኦል ይሄዳል፡፡ ”አናርፒታ ቻሪም ቺራት“ ሰለዚህም ሁልግዜ የሩፓ ጎስዋሚን ትእዛዝ ማስታወስ ይገባናል፡፡ ሰለዚህም ሁል ግዜ እንዲህ በማለት እንፀልያለን፡፡ ”ሽሪ ቼይታንያ ማኖ ቢሽታም ስታፒታም ዬና ብሁታሌ“ የእኛም ተልእኮ የሺሪ ቼይታንያ መሀብራብሁን ፍላጎት ለሟሟላት ነው፡፡ ይህን ነው የእኛ ሀላፊነት፡፡ ”ሺሪ ቼይታንያ ማኖ ቢሽታም ስትሀፒታም ዬና ብሁታሌ“ ሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚ ይህንን አከናውኖታል፡፡ ብዙ መፃህፍቶችንም አቅርቦልናል፡፡ በተለይ ”ብሀክቲ ራሳ አምርታ ሲንድሁ“ የተባለውን፡፡ ይህንንም መፅሀፍ ወደ እንግሊዘኛ ”ኔክታር ኦፍ ድቮችን“ ብለን ተርጉመነዋል፡፡ ይህም የትሁት አገልግሎት ስርዓት ሳይንስን ያስረምረናል፡፡ ይህም የሩፓ ጎስዋሚ ትልቁ አስተዋተዋፅኦ ነበረ፡፡ ይህም እንዴት ትሁት አገልጋዮች እንደምንሆንን በማስተማር ነው፡፡ እንዴት የፈጣሪ አምላክ ትሁት አገልጋይ እንደምንሆን መማር ስሜታዊ ሳይሆን ሳይንሳዊ ስርዓት ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር በሳይንሳዊ አመራር የተመሰረተ ነው፡፡ ”ያድ ቪግያና ሳማንቪታም ግያናም ሜ ፓራማም ጉህያም ያድ ቪህያና ሳማቪታም“ ይህም ስርዓት ስሜታዊ ብቻ አይደለም፡፡ ይህም ስርዓት እንደ ስሜታዊ ብቻ ካያችሁት ረብሻ ልታመጡ ትችላላችሁ፡፡ ይህ የሩፓ ጎስዋሚ ትእዛዝ ነው፡፡ እንዲህም ብሎናል ”ሽሩቲ ስምርቲ ፑራናዲ ፓንቻራትርኪ ቪድሂም ቪና አይካንቲኪ ሃሬር ብሃክቲር ኡትፓታያይቫ ካልፓቴ“ (ብሰ 12 101)