AM/Prabhupada 0215 - ካነበናችሁ መረዳት ትችላላችሁ፡፡



Interview with Newsweek -- July 14, 1976, New York

ቃለ መጠይቅ:ስለ ህይወትህ ትንሽ ልትነግረን ትችላለህ?ልጅ ሁነህ እያለህ:ምን አይነት ነገሮች ታደርግ ነበር? ፕራብሁፓዳ:ለምን እነግርሻላሁ?ቃለ መጠይቅ:ምን አልከኝ? ፕራብሁፓድ:ለምን እነግርሻለሁ:ቃለ መጠይቅ:ፍላጎትህ ከሆነ: ፕራብሁፓድ:ለምን ፍላጎቴ ይሆናል? ቃለ መጠይቅ:እኛ ይህንን መጠየቅ አለብን:አለበለዘ ከስራ እንወጣለን: ሀሪ ሶሪ:ፕራብሁፓድ ተሰፋ ያለው:ስለ ስራው የሚጠቅም ጥያቄ እንድትጠይቂው ነው: ራሜሽቫራ:ሰዎች ስለ አንተ መረዳት ይፈልጋሉ ሽሪላ ፕራፕሁፓድ: ስለ አንተ ፍላጎት ከአደረባቸው:ስለ መጽሃፍህም ፍላጎት ያድርባቸዋል: ይህን ሁሉ መጽሃፍት ስለ የምንሸጥለት ደራሲ:ማወቅ ይፈልጋሉ: ፕራብሁፓድ:መጻህፍት? ስለ መፃህፍቱ ማውራት እንችላለን: ነገር ግን:ማን በፊት ደራሲ እንደነበረ ይወስናል? ቃከ መጠይቅ:እንደምረዳው:አንተ ነህ እነዚህን መፃህፍት የተረጎምካቸው: ፕራብሁፓድ:አዎን:እና ይህም ትርጉም የሰጠሁት:መፅሀፉ እንዴት እንደተረጎምኩት ይነግራችኋል: ቃለ መጠይቅ:እኔ ያሰብኩት ፕራብሁፓድ:መጽሃፉን አንብቢ ከዛም ትረጃለሽ: እኔን ጥያቄ ከመጠየቅ:መጽሀፉን ብታነቢ ይሻላል: ያ ትክክለኛ መረጃ ነው: ቃለ መጠይቅ:እኔ ለመጠየቅ የፈለግሁት:እንዴት ፍላጎት እንዳደረበት እና:እንደ ጀመረ:እዚህ ለመድረስስ ምን እንደገፋፋው ነው: ራሜሽቫራ:ተረዳሁ:እርሷ የምትጠይቀው:ከጉሩ ማሃራጅህ ጋር የነበረውን ግኑኝነት ነው: እንዴት እንደተነሳሳህ እና እንዴት እንቅስቃሴውን ጀምረህ:ብዙ መጽሀፍ እንደጻፍክ ነው: ፕራብሁፓድ:ይህን አንተ መመለስ ትችላለህ:ለህዝብ አስፈላጊ የሆነ ጥያቄ አይደለም: ራሜሽቫራ:እንደተረዳሁት:ህዝብ ሁልግዜ ከእንቅስቃሴው ጀርባ ስለአለው ሰው መረዳት ይፈልጋል: ሴት እንግዳ:አዎን:ይረዳናል:ህዝብም ማወቅ ይፈልጋል: ህዝብ ሰለ እንደ አንተ እድገት ማወቅ ይፈልጋሉ:ምክንያቱም በቀላሉ ሊረዱት ስለሚችሉ ነው: እንደዚሁም ሁሉ መጽሃፍህን ለማንበብ ውሳኔ ያደርጋሉ: ፕራብሁፓድ:በመጀመሪያ ደረጃ:ስለ እኛ መጽሀፍት ፍላጎት ካደረብሽ ማንበብ አለብሽ:እንደዚህም በማድረግ ትረጃለሽ: ቃለ መጠይቅ:አንተን መረዳት እንችላለን? ፕራብሁፓድ:አዎን: ቃለ መጠይቅ:እንዲህ ነው የምትለው? ፕራብሁፓድ:አዎን: ቃለ መጠይቅ:እንዲህ ማለቱ ነው? ፕራብሁፓድ:ሰው የሚታወቀው ሲናገር ነው:ሲናገር: ”ታቫክ ቻ ሾብሃቴ ሙርኮ ያቫትኪንቺን ና ብሃሳቴ“ “ሞኝ መናገር እስኪጀምር ድረስ:አዋቂ ይመስላል” ሲናገር ግን:ማን እንደሆነ ታውቁታላችሁ: የእኔ ንግግር ሁሉ መጽሀፌ ውስጥ አለ:አዋቂ ከሆንሽ ደግሞ ልትረጂው ትችያለሽ: መጠየቅም አያስፈልግሽም: ልክ እንደ ህግ ቤት:ዳኛው ሊታወቅ የሚችለው ሲናገር ነው: አለበለዛ ግን ሁሉም አዋቂ ዳኛዎች ይመስላሉ: ነገር ግን በፍርድ ቤት ውስጥ መናገር ሲጀምር:ጥሩ ወይንም መጥፎ ዳኛ መሆኑን ሁሉም ሊረዱ ይችላሉ: ስለዚህ መስማት ያስፈልጋል:ማንበንብ ያስፈልጋል:ከዚያም ልትረዱ ትችላላችሁ: በትክክለኛ ለመረዳትም ይቻላል: