AM/Prabhupada 0227 - ለምንድነው የምሞተው



Lecture -- Los Angeles, May 18, 1972

ክርሽናን በትክክል ለመረዳት ትንሽ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በመሰረቱ አብዩ አምላክን ለመረዳት የሚያሰፈልገው እውቀት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን አብዩ አምላክ እራሱ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ሰለ እራሱ በደንብ ተንትኖ ገልፆልናል፡፡ “እኔ እንዲህ ነኝ፡፡ ይህም ቁሳዊ ዓለም እንዲህ ነው፡፡ መንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ነው፡፡ ነፍሳት እንዲህ ናቸው፡፡” ወዘተ ሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልፆ ይገኛል፡፡ አብዩ አምላክ እራሱ በሰጠው እውቀት ብቻ ነው ሰለ አብዩ አምላክ በትክክል ሊያስረዳን የሚችለው፡፡ አለበለዛ ግን ሰለ አብዩ አምላክ ማንነት በመገመት ልንረዳው አንችልም፡፡ ይህም የማይቻል ነገር ነው፡፡ እርሱ ወሰን የለውም እኛ ግን ወሰን ያለን ነን፡፡ እውቀታችንም ሆነ አስተሳሰባችን ሁሉ በጣም የተወሰነ ነው፡፡ ታድያ እንዴት አድርገን ወሰን የሌለውን ለመረዳት እንችላለን? ነገር ግን ወሰን የሌለው የሚሰጠንን መልእክት እና ስለ እርሱ ማንነት ብንማር እርሱን በደንብ ልንረዳው እንችላለን፡፡ ይህ ፍጹም የሆነ እውቀት ነው፡፡ ስለ አብዩ አምላክ በመገመት ምንም ዋጋ ያለው እውቀት ልናገኝ አንችልም፡፡ ትክክለኛ እውቀት ማለት.... አንድ ምሳሌ ልስጣችሁ ለምሳሌ አንድ ትንሽ ልጅ ሰለ አባቱ ለማወቅ ከፈለገ ቀላሉ መንገድ እናቱን ሂዶ መጠየቅ ብቻ ነው፡፡ እናቱም እንዲህ ትለዋለች “ይህ አባትህ ነው፡፡” ይህ ትክክለኛ እውቀት ነው፡፡ ነገር ግን ግምት ውስጥ ቢገባ ግን “አባቴ ማነው?” እያለ መላ ከተማውን ደጋግሞ ቢጠይቅ “አንተ አባቴ ነህ?” ይህ አይነቱ እውቀት ትክክለኛ ላይሆን ይችላል፡፡ በዚህ መንገድም ትክክለኛ አባቱን ለይቶ ለማረጋገጥ ያዳግተዋል፡፡ ነገር ግን በዚህ ቀላል ስርዓት ሰለ አባቱ በቀላሉ ስልጣን ካላት ከእናቱ ቢረዳ “ልጄ ሆይ አባትህ ይህ ነው” ትለዋለች፡፡ ይህም እውቀት ትክክለኛ ይሆናል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መንፈሳዊ እውቀት ..... ቀደም ብዬ እንደተናገርኩት መንፈሳዊ ዓለም አለ ብያለሁ፡፡ ይህም በግምት ያገኘነው እውቀት አይደለም፡፡ ነገር ግን አብዩ ፈጣሪ አምላክ እርሱ ሲነግረን “መንፈሳዊ ዓለም አለ፡፡ ይህም የእኔ ዋናው መኖርያ ነው፡፡” ብሎ ሲነገረን ይህ ትክክለኛ እውቀት ነው፡፡ ሰለዚህ እውቀት የምናገኘው ከክርሽና ነው፡፡ እርሱም ከሁሉም በላይ የሆነ ባለሥልጣን ነው፡፡ በዚህም ስርዓት እውቀታችን ፍፁም ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ በስራችን ፍፁም ላንሆን እንችላለን እውቀታችን ግን ፍፁም ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም የምንወስደው እውቀት ፍፁም ከሆነው ከአብዩ ጌታ በመሆኑ ነው፡፡ ልክ ቀደም ብሎ ምሳሌ እንደተሰጠው አባቴ ማን እንደሆነ ትክክለኛውን እውቀት ላላገኝ እችላለሁ፡፡ እናቴ ግን ትክክለኛው እቀቀቱ አላት፡፡ ከእናቴም ትክክለኛውን እውቀት በመቀበሌ ሰለ አባቴ ማንነት በትክክል ለመረዳት በቀቻለሁ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር የተሰማራው ይህንን ፍፁም የሆነውን እወቀት ለሰው ልጅ ሕብረተሰብ ለማስተማር ነው፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ፡፡ አብዩ አምላክ ማን እንደሆነ፡፡ ይህ ቁሳዊ ዓለም ምን እንደሆነ፡፡ ወደ እዚህስ ቁሳዊ ዓለም ለምን እንደመጣን ለምንስ ብዙ ስቃይ እና መከራ በዚህ ዓለም ላይ እንደምናይ ለምን ሕይወት ብዙ ዓይነት መከራን እንደምታሳያን ለምን እንደምንሞት ያሰተምረናል፡፡ መሞት አልፈልግም ነገር ግን ሞት ግዳጄ ነው፡፡ ለማርጀት አልፈልግም ነገር ግን ይህ ግዳጄ ነው፡፡ በበሽታም መሰቃየት አልፈልግም ነገር ግን ከዚህ መራቅ አልችልም፡፡ እነዚህ አይነት ችግሮች ናቸው መፈታት የሚገባቸው፡፡ ይህ ነው የሰው ልጅ ዋነኛው ችግሩ፡፡ ትልቁ ችግራችን ይህንን የተመቻቸ የመብላት የመተኛት የወሲብ እና የመከላከል ስርዓቶችን ማስተካከል አይደለም፡፡ ይህ የሰው ልጅ ኑሮ ዓላማ አይደለም፡፡ ሰውም ይተኛል ውሻም ይተኛል፡፡ ቢሆንም ግን ገና ለገና የሰው ልጅ በአማረ አፓርትመንት ውስጥ ኖረና ከውሻ የተሻለ አያደርገውም፡፡ ዋናው ዓላማው መተኛት ነው፡፡ ይኀው ነው፡፡ ገና ለገና የሰው ልጅ አቶሚክ ቦንብ ፈጠረና ውሻ ደግሞ በጥርሱና በጥፍሩ ታገለና የበታች ነው ማለት አይደለም፡፡ ውሻም እንደሰው ልጅ እራሱን መከላከል ይችላል፡፡ ዋናው ዓላማ መከላከል ነው፡፡ ገና ለገና አቶሚክ ቦንብ ፈጥሬአለሁ እና መላ ዓለምን ወይንም ትእይንተ ዓለምን ማሸነፍ እችላለሁ ብለን ማሰብ አንችልም፡፡ ይህ አይቻልም፡፡ እናንተ በራሳችሁ መንገድ መከላከል ትችላላችሁ፡፡ ውሻውም በእራሱ መንገድ መከላከል ይችላል፡፡ ሰለዚህ ይህ ያማረ ዓይነት መከላከል ወይንም ያማረ ዓይነት አበላል ያማረ ዓይነት እንቅልፍ ወይንም ያማረ ዓይነት የወሲብ ግኑኝነት አንድ ሰውን ወይንም አንድ የአገርን ግዛት የሰለጠነ ሊያደርገው አይችልም፡፡ ይህ የስልጣኔ ምልክት አይደለም፡፡ ሁሉም ዓላማው አንድ ነው፡፡ ሲመዛዘን የመቶም ሆነ የሁለት ሺህ ወይንም የሀያ ቁጥሮች አምስት በመቶ ቢወሰድ ሬሾው ሁሉ አንድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሰለዚህ ይኅው የእንስሶች ዓይነት ኑሮ በተወለወለ እና በሳይንቲፊክ መንገድ አደረጀነው እና የሰለጠንን የሰው ልጅ ሕብረተሰብ አያደርገንም፡፡ ይህም የተወለወለ የእንስሳ ኑሮ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ትክክለኛው ስልጣኔ አብዩ አምላክን ማወቅ ነው፡፡ ይህ የተራመደ ሕብረተሰብ ምልክት ነው፡፡