AM/Prabhupada 0238 - ዓብዩ ጌታ ጥሩ ነው፡፡ እርሱ ፍፁም ጥሩ ነው፡፡



Lecture on BG 2.3 -- London, August 4, 1973

"አታሀ ሽሪ ክርሽና ናማዲ ና ብሀቬድ ግራህያም ኢንድሪያሀ“ (ቼቻ ማድህያ 17 136) ታድያ ይህንን የመሰለ የሽሪ ክርሽናን ባህርይ እንዴት ተራ ሰዎች ሊረዱት ይችላሉ? ምክንያቱም ያላቸው ተራ እና ፍፁም ያልሆነ ስሜቶቻቸው ለስህተት ሰለሚያጋልጧቸው ነው፡፡ ክርሽናን የእራሱ ትሁት አገልጋይ ወይንም ቫይሽናቫ እንኳን ላይረዳው ይችላል፡፡ ይህም ተገልጿል፡፡ ”ቫይሽናቬራ ክሪያ ሙድራ ቪግነሀ ና ብሁጅሀያ (ቼቻ ማድህያ 17 136) የቫይሽናቫ አቻርያ (መምህር) እንኳን ክርሽናን ላይረዳው ይችላል፡፡ በጣም በእውቀት የላቀ እና ብስለት ያለው ሰውም ቢሆንም ክርሽ የሚያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ላይረዳ ይችላል፡፡ ሰለዚህም ከፍተኛ ባለስልጣኖችን መከተል እንጂ ለማስመሰል ጥረት ማድረግ አይገባንም፡፡ ትእዛዛቸውን መከተል ይገባናል፡፡ ይህም ማለት በባለስልጣኖች የተሰጠውን መመሪያ መከተል ማለት ነው፡፡ አለበለዛ ክርሽናን ለመረዳት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ክርሽና በጦር ሜዳው ላይ አርጁናን እንዲዋጋ ይገፋፋው ነበር፡፡ ይህም ማለት እኛም ሌሎች እንዲዋጉ መገፋፋት አለብን ማለት አይደለም፡፡ ይህም አግባብ ያለው አይሆንም፡፡ ለክርሽና ግን ይህ አግባብ የሌለው አይደለም፡፡ አብዩ የመላእክት ጌታ የሚያደረገው ነገር ሁሉ ጥሩ ነው፡፡ እርሱ ፍፁም ጥሩ የሆነ አብይ አምላክ ነው፡፡ ያለ ጥርጣሬ መቀበል አለብን፡፡ የሚያደረገው ነገር በሙሉ ፍፁም ጥሩ ነውና፡፡ ይህ መልካም ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ስልጣን የሌለውን ትእዛዝ መከተል መጥፎ ተግባር ነው፡፡ አብዩ አምላክ ግን ከማንም ቢሆን ትእዛዝ መቀበል አያስፈልገውም፡፡ “ኢሽቫራ ፓራማ ክርሽና” (ብሰ፡ 5 1) ከማንም ቢሆን መመሪያ ለመቀበል አያስፈልገውም። የሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍፁም ጥሩ ነው፡፡ ክርሽናን ለመረዳት የምንችለው በዚህ መሰረት ነው፡፡ ክርሽናን በራሳችን ግምት ለመረዳት አንችልም፡፡ ክርሽና በእናንተ ምርምር እና ፈተና ሊገለፅ የሚችል ወይንም ሊፈተን የሚገባው አይደለም፡፡ እርሱ ከሁሉም በላይ ነው፡፡ እርሱ ከቁሳዊው ዓለም ተሻግሮ የሚገኝ ንፁህ መንፈሳዊ አካል ነው፡፡ ስለዚህ የመንፈሳዊ አለመካከት የሌላቸው ሁሉ ክርሽናን በትክክል አይረዱትም፡፡ በጦር ሜዳውም ላይ አርጁና እንዲዋጋ እያበረታታው ነው፡፡ “ክላይብያም ማ ስማ ጋማሀ ፓርትሀ ናይትሀት ትቫዪ ኡፓፓድያቴ ክሱስራም ህርዳያ ዶርባልያም ታክትቮቲስትሀ ፓራንታፓ” (ብጊ፡2 3) ፓራንታፓ የሚለውን ቃል ክርሽና እንዲህ ለማለት ተጠቀመ “አንተ ክሻትርያ ነህ፡፡ አንተ ንጉስ ነህ” የአንተ ስራ አታላዮች እና ቀጣፊዎችን መቅጣት ነው፡፡ ይህ ነው ተግባርህ፡፡ እነዚህንም አታላዮች እና ቀጣፊዎች ምህረት ልታደርግላቸው አይገባም፡፡ ከዚህ ቀደም ነገስታት ሁሉ እንደሚያደርጉት ማለት ነው፡፡ ንጉስ እራሱ ፍርድ ውስጥ የሚገባበት ግዜ ነበረ፡፡ ወንጀለኞች በንጉሱ ፊት ይቀርቡ ነበረ፡፡ ንጉሱም ይገባዋል የሚል እውቀት እና መረጃ ካለው የገዛ እራሱን ጎራዴ አውጥቶ የወንጀለኛውን ጭንቅላት ይቆርጠው ነበረ፡፡ የንጉሱም ስልጣን እና ሀላፊነት እንዲህ ነበረ፡፡ በብዛት ባይታይም ከመቶ ዓመት በፊት በካሽሚር ውስጥ ለነበረው ንጉስ ሌባ በተያዘ ግዜ በንጉሱ ፊት ይቀርብለት ነበረ፡፡ የዚህም ሰው ሌባ መሆን እና መስረቁም ከተረጋገጠ ንጉሱ በቀጥታ የሌባውን እጅ እራሱ ይቆርጠው ነበረ፡፡ ይህም ከመቶ ዓመት በፊት ነበረ፡፡ በዚህም መንገድ ሌሎች ሌባዎች ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸው ነበረ፡፡ "ይህ ነው ቅጣታችሁ፡፡" በዚህም ምክንያት ሌብነት ጠፍቶ ነበረ፡፡ መስረቅ እና መዝረፍ በካሽሚር ውስጥ ጠፍቶ ነበረ፡፡ አንድ ሰው መነገድ ላይ እቃ ጥሎ ቢሄድ እንኳን የሚነካው ሰው አልነበረም፡፡ ማንም ሰው እቃውን አይወስደውም ነበረ፡፡ የንጉሱም ትእዛዝ እንዲህ ነበረ፡፡ "በመንገድ ላይ ወድቆ የሚገኝ የሰው እቃ ማንም ሰው አንስቶት ሊወስድ አይችልም፡፡" እቃውን የጣለው ሰው መጥቶ መውሰድ አለበት እንጂ ሌላ ሰው እቃውን ለመውሰድ አይገባውም፡፡" መቶ ዓመት በፊት እንዲህ ነበረ፡፡ ሰለዚህ እንዲህ ዓይነቱ ዓብይ ቅጣት አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ግን እንደዚህ ዓይነት አብይ ቅጣፎች ቀርተዋል፡፡ ሰው ገዳዮችም አይሰቀሉም፡፡ ይህም ስህተት እና ተንኮለኝነት ነው፡፡ ሰው ገዳይ ያለ ምህረት መገደል አለበት፡፡ ለምን ሰው የሚገድል ብቻ? እንስሳም የሚገድል እንኳን መሰቀል ይገባዋል፡፡ ይህ ነበር የቀድሞው የነገስታት ስርዓት፡፡ ንጉሱ በጣም ጥብቅ የሆነ አመራት እንዲኖረው ያሰፈልጋል፡፡