AM/Prabhupada 0419 - ድቁና ማለት የክርሽና ንቃታችሁ 3ኛ ደረጃ ማለት ነው፡፡



Lecture & Initiation -- Seattle, October 20, 1968

ይህ የድቁና ስርዓት ማለት የክርሽና ንቃት የሶስተኛው ደረጃ ማለት ነው፡፡ እነዚህም በድቁና ስርዓት በመሰማራት የሚገኙት ሁሉ የተደነገጉትን የክርሽና ንቃት ሕግጋት እና መመሪያ በትክክል መከተል አለባቸው፡፡ ልክ ከበሽታ ለመዳን እንደሚፈልግ በሽተኛ ሀኪም የሚሰጠውን ትእዛዝ በጥሞና መከታተል አለበት፡፡ ከበሽታውም በቶሎ እንዲድን ሊያደርገው የሚችለው ይኅው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን አራቱን መመሪያዎች በትክክል መከተል ያሰፈልጋችኃል፡፡ 16 ዙርያም የክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህንንም ስርዓት በመከተል ቀስ በቀስ በዚህ በመነሳሳት ለክርሽና ንቃት ጣእሙ እና ቅርበቱ እያደገ ይመጣል፡፡ ከዚያም የክርሽና ፍቅር አውቶማቲካሊ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም ፍቅር በልባችን ውስጥ ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ ይህ ለክርሽና ያለን ፍቅር ከውጪ የሚመጣ አስገድደን የምናመጣው ነገር አይደለም፡፡ ይህም ሁሉ ቦታ እና ከሁሉም ፍጥረታት ጋር ያለ ነው፡፡ አለበለዛም በውስጣቸው ባይኖር ኖሮ እንዴት እነዚህ አሜሪካን ልጆች እና ልጃገረዶች ሊያነቃቁት ቻሉ? ይህም ፍቅር በውስጣችን ያለ ነው፡፡ እኔ በማነቃቃት ብቻ እየረዳሁ እገኛለሁ፡፡ ልክ እንደ ክብሪት፡፡ ክብሪት እሳት አለው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው መጫር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ እሳት በውስጡ ያለ ነው፡፡ ሁለቱን እንጨቶች ብቻ በማነካካት እሳት ላይገኝ ይችላል፡፡ ይህም የእሳቱ ኬሚካል ከላይ ባይኖር ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና ንቃት በሁሉም ልብ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የሚያስፈልገው ግን በክርሽና ንቃት ማህበር በመሳተፍ ይህንን ፍቅር ማነቃቃት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ሰለዚህ ይህ አስቸጋሪም ሆነ ተግባራዊ ወይንም የማያጓጓ ያልሆነ አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ሰለዚህ ሁሉንም የምንጠይቀው ነገር ቢኖር ይህንን በጣም ምህረታዊ የሆነውን የጌታ ቼታንያን ስጦታ ተቀበሉ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃትን እና የሀሬ ክርችናን ቅዱስ ስም የመዘመርን ነው፡፡ በዚህም በጣም ደስተኞች ትሆናላችሁ፡፡ ይህ ነው ፕሮግራማችን፡፡ እናመሰግናለን፡፡