AM/Prabhupada 0444 - ጐፒዎች በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ውስን የሆኑ ነፍሳት ሳይሆኑ በንፁህ መንፈሳዊነታቸው ነፃ የሆኑ ናቸው፡፡



Lecture on BG 2.8-12 -- Los Angeles, November 27, 1968

ፕራሁፓድ:ህምምም?

ድቮቲ:አንድ ቦታ የፃፍከውን አንብቤ ነበረ: ስለ ራድሃ ክርሽና ሚስትራዊ እውቀትን ስለማወቅ: አንድ ሰው ጎፒዎችን ማገልገል አለበት:ጎፒዎችም የጎፒዎች አገልጋዮች ናቸው: እና አንተም የጎፒዎች አገልጋይ ነህ ብዬ አስብኩ: ይህ ትክክል ነውን? ወይንም እንዴት አድርገን ነው የጎፒዎቹን አገልጋዮች ለማገልገል የምንችለው?

ፕራብሁፓድ:ጎፒዎች በዚህ አለም እንደኛ የተወሰኑ ነፍሶች አይደሉም: እነርሱ ነፃ የወጡ ነፍሶች ናቸው: በመጀመሪያ ደረጃ:አንተ ከዚህ ከአለማዊ ውስን ኑሮ መውጣት አለብህ: ከዛም ጎፒዎቹን የማገልገል ጥያቄ ይመጣል: በአሁኑ ግዜህ ጎፒዎችን በቀጥታ ለማገልገል አትሻ: ከዚህ አለማዊ ውስን ኑሮ ግን ለመውጣት ሞክር: ከዚያም ጎፒዎቹን ለማገልገል የምትችልበት ግዜ ይመጣል: በዚህ በአለማዊ የወተሰነ ኑሮአችን:ማገልገል አንችልም:ክርሽና እያደረገው ነው: ነገር ግን:ክርሽና በ”አርቻ ማርጋ“ አማካኝነት እድሉን ሰጥቶናል: ልክ ለክርሽና ደይቲ ፕራሳድ እንደምናቀርብለት:መመሪያችንን እየተከተልን: እንዲህም መግፋት አለብን:መዘመር እና መስማት: ቤተ መቅደስም መስገድ:አራቲ እና ፕራሳድም ማቅረብ: እንዲህ እያደረግንም ስንራመድ:ክርሽና ሁሉን ሊከፍትልን ይችላል: የራሳችሁንም ሁኔታ ምን ላይ እንዳለ ትረዱታላችሁ: ጎፒዎች ማለት ሁልግዜ አምላክን በማገልገል ላይ የሚገኙ ማለት ነው: ይህም የዘላለማዊ ግኑኝነት ወደፊት ይገለጻል:መጠብቅም አለብን: ወዲያውኑ ግን እንደጎፒዎቹ ለመምሰል አይገባንም ጎፒዎችን ለማገልገል ጥሩ ሃሳብ ነው:ነገር ግን ይህ ብዙ ግዜ ይፈልጋል:ወዲያውኑ አይሆንም: አሁን ወዲያውኑ ማድረግ ያለብን ግን:ህግጋት እና መመሪያችንን መከተል እና ሃላፊነታችንን መወጣት ብቻ ነው: