AM/Prabhupada 0494 - ናፖሊዎን ታላላቅ እና ጠንካራ የከተማ መግቢያ ሰርቶ ነበር፡፡ ታድያ አሁን በየት ይገኛል



Lecture on BG 2.14 -- Germany, June 21, 1974

”አንያትሀ ሩፓም“ ማለት መኖር ወይንም አለመኖር አለመኖር ማለትም እኔ ነፍስ ሰለሆንኩኝ የመንፈሳዊ ገላ አለኝ፡፡ ነገር ግን በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ባሉት ፍላጎቶቼ የተነሳ አንዳንድ ግዜ የሰው ልጅ ገላን እይዛለሁ አንዳንድ ግዜ ደግሞ የውሻን ገላ ልይዝ እችላለሁ፡፡ አንዳንድ ግዜም የድመት ገላ አንዳንዴ የዛፍ ገላ አንዳንዴ ደግሞ የመላእክት ገላ። ወደ 8,400,000 የሚሆኑ የተለያዩ ፍትረታት ገላዎች በዚህ ትእይንተ አለም ይገኛሉ፡፡ የእያንዳንዳችንም ገላ ካለን የቁሳዊ ዓለም ፍላጎት አንፃር እየተቀያየረ ይገኛል፡፡ የዚህም ገላ መቀያየር የሚወስነው ምን ያህል በዚህ ቁሳዊ ዓለም እንደተበከልን ነው፡፡ “ካርማናም ጉና ሳንጋ አስያ” የሚወስኑትም እነዚህ ስውር የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ትክክለኛ እውቀቱ ይኅው ነው፡፡ ይህንንም መከታተል እንጂ ለግዜያዊ ደስታ ቁሳዊ ነገሮችን መፈልሰፍ አይደለም። ይህም ሞኝነት ነው፡፡ ይህም ግዜን የሚያጠፋ ሞኝነት ነው፡፡ ለዚህ ገላ ምቾት አንዳንድ ነገሮችን የምንፈጥር ብቻ ከሆነ ለግዜው ምቾት ሊሰማን ይችላል ነገር ግን “በምቾት ሁሌ ለመኖር አይፈቀድልህም፡፡” በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በጣም ቆንጆ እና በጣም ጠንካራ ቤት ሰርቶ ይሆናል፡፡ ይህም በጥንካሬ የማይወድቅ ተደርጎ ተሰርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ለእራስህ ምን አድረገሀል፡፡ ይህም እራስህን እንደማትሞት አድረገህ ይህንን ቤት እንድትደሰትበት ምን ዝግጀት አድረገሀል? "ይሁን እርሱ እንደ አለ ይሁን፡፡ ነገር ግን አንድ ጠንካራ ቤት ልገንባ፡፡“ በመጨረሻም ቤቱ ቀሪ ይሆናል፡፡ አንተም ትሄዳለህ፡፡ ልክ እንደ ናፖሊዮን፡፡ እርሱም ብዙ ጠንካራ ህንፃዎችን ሰርቶ ነበረ፡፡ ነገር ግን ወዴት ሄደ? ማንም ሊያውቅ አይችልም፡፡ ስለዚህም ብሀክቲቪኖድ ታኩር እንዲህ ብሎ ዘምሯል፡፡ ጃዳ ቢድያ ያቶ ማያራ ቫይብሀቫ ቶማራ ብሃጃኔ ባድሀ በቁሳዊው ዓለም የደስታ ፍላጎት እና እርምጃ በገፋን ቁጥር የእራሳችንንም ማንነት እንደዚሁ እየዘነጋን እንመጣለን፡፡ ይህ ነው ውጤቱ፡፡ ስለዚህ እኛ ልዩ ወይንም የተለየ እና ትክክለኛ ስራ እንዳለን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ይህም ራስን የማወቅ ጥናት ይባላል፡፡ ”እኔ ይህ ገላ አይደለሁም“ ይህ እራስን የማወቅ ነው፡፡ ይህም በክርሽና በመጀመሪያ ደረጃ ተገልጾልናል፡፡ ይህም ”አንተ ይህ ገላ አይደልህም፡፡“ ብሎ ነው፡፡ ይህም የመንፈሳዊ የመጀመሪያ እውቀት ነው። የመጀመሪያውም የመንፈሳዊው እውቀት ”ይህ ገላዬ ማለት እኔ አይደለሁም፡፡ እኔ መንፈሳዊ ወይንም ነፍስ ነኝ፡፡ በዚህ ዓለም ላይም የተለየ ዓላማ አለኝ፡፡“ ይህም የሰው ልጅ ዓላማ በዚህ ጊዝያዊ ስራ ላይ መሰማራት እንደ ውሻ ወይም ዓለማዊ የሰው ልጅ መሰማራት አይደለም፡፡ ወይም እንደ ነብር እንደ ዛፍ እንደ አሳ መኖር አይደለም፡፡ “አሀራ ኒድራ ብሀያ ማይትሁናም ቻ” ይህም የስጋዊ አካል ዋነኞቹ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ መብላት መተኛት በወሲብ መሰማራት እና እራሳችንን መከላከል ነገር ግን በዚህ በሰው ልጅ ትውልድ እኔ የተለየ ስራ አለኝ፡፡ ይኅውም እራስን የማወቅ ጥናት ነው፡፡ ይህም የሚረዳን ከዚህ ከቁሳዊው ዓለም መወሳሰብ እንድንወጣ ነው፡፡ ይህም ትክክለኛ እውቀት ይባላል፡፡ ያለዚህ እውቀት ግን ምንም ዓይነት እውቀትን ብናስፋፋ ይህ እንደ ሞኝነት ይቆጠራል፡፡ ሽራማ ኤቫ ሂ ኬቫላም (ሽብ፡ 1.2.8)