AM/Prabhupada 0527 - ለሽሪ ክርሽና በፍቅር አገልግሎታችንን በማቀረብ ሊጐልብን የሚችል ነገር አይኖርም፡፡ እዲያውም ሊጨመርልን ይችላል፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Los Angeles, December 2, 1968

ፕራብሁፓድ፡ ጥያቄዎች አላችሁን? ጃያ

ጐፓል፡ ፕረሳዳም ወይምን መንፈሳዊ ምግብን ከምንወደው ሰው መቀበል አንዱ የፍቅር መለዋወጥ መግለጫ ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን አንተም አቅርብም ተቀበልም፡፡ ዳዳትሂ ፕራቲግርህናቲ ብሁንክቴ ብሆጃያቴ ጉህያም አክህያቲ ፕርቻቲ ቻ ሀሳብህን ለክርሽና ስትገልፅ ክርሽና ደግሞ መንገዱን ያሳይሀል፡፡ አየህ? ለክርሽናም አቅርብለት፡፡ “ክርሽና ሆይ ብዙ ጥሩ ነገሮች አቅርበህልናል፡፡ ይህንንም ያቀረብንልህን ምግብ ቅመስልን፡፡ ከዚያም እኛ በአክብሮት እንመገበዋለን፡፡” ክርሽና በዚህ በጣም ደስተኛ ይሆናል፡፡ይኅው ነው፡፡ ክርሽና በፍቅር ያቀረብንለትን ይመገባል፡፡ ያቀረብንለትንም እንደ አለ መልሶ ይተውልናል፡፡ ፑርናስያ ፑርናም አዳያ ፑርናም ኤቫቫሺሽያቴ (ኢሾፓኒሻድ መነሻ ትቅስ) ለክርሽና ስናቀርብለት እንዲህ ማለት አይደለም... ክርሽና ያቀረብንለትን ምግብ ይመገባል፡፡ ነገር ግን ክርሽና ሁልግዜ ሙሉ እና የረካ ነው፡፡ የቀረበለትን ሁሉ እንደ አለ ይተውልናል፡፡ ሰዎች ይህንን በትክክል አይረዱም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ለክርሽና ምግብ አዘጋጅቶ በማቅረብ የሚጐድልብን ነገር አይኖርም፡፡ እኛ ግን ተጨማሪ ነገር ከክርሽና እናገኛለን፡፡ (በረከት) ክርሽናን ቆንጆ አድርጋችሁ ታለብሱ ታሸበርቁ እና ቁንጅናውን ታዩታላችሁ፡፡ ከዚያም ቆንጆ ነገር የማየቱ ፍላጐታችሁ የተሳካ ይሆናል፡፡ ይህንንም በማየት በዓለም ላይ ቆንጆ የሚባሉትን ነገሮች ለማየት ጉጉት አይኖራችሁም፡፡ ክርሽናን ሁልግዜ በተመቸው እና በሚደሰትበት ደረጃ ስታስቀምጡት ክርሽናም እንደዚሁ የተመቸ ቦታ ያስቀምጣችኋል፡፡ ለክርሽና በጣም ጥሩ የሆነ ምግብ ስትሰጡ እናንተም ጥሩ የሆነውም ምግብ ትመገባላችሁ፡፡ ለምሳሌ ፊቴን ብኩለው እንዴት ቆንጆ እንደሆነ ለማየት አልችልም፡፡ ነገር ግን አንድ መስታወት ባመጣ ፊቴ ቆንጆ እንደሆነ ለማየት እችላለሁ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛ የክርሽና ስስሎች ነን፡፡ የሰው ልጅ የተፈጠረው በአብዩ አምላክ ምስል ነው፡፡ ስለዚህ ክርሽናን ለማስደሰት ከቻልን እኛም የክርሽና ምስሎች ደስተኞች ለመሆን እንችላለን፡፡ ክርሽና እራሱን ለማስደሰት የእኛ አገልግሎት አያስፈልገውም፡፡ እርሱ ራሱ ሙሉ በሙሉ የረካ ነው፡፡ ነገር ግን ክርሽናን ብናቀርብለት እና ልናስደስተው ከሞከርን እኛ ራሳችን ልንደሰት እንበቃለን፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ስለዚህ ክርሽናን ለማሸብረቅ እና ሁሉንም ምግብ በመስራት ልታቀርቡለት ሞክሩ፡፡ ክርሽናንም ሁልግዜ የሚያመቸው ደረጃ ላይ አስቀምጡት፡፡ በዚህም መንገድ በምናቀርብለት ነገር በሙሉ ልውውጥ ይኖረናል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡ የቁሳዊ ዓለም በሽታ ልክ እንደ ውሻ ጭራ ይቆጠራል፡፡ አይችሁ የውሻው ጭራ እንዲህ ይመስላል፡፡ (ወደላይ የተቀለበሰ) ምንም እንኳን ዘይት ብናደርግበት እና ቀጥ ለማድረግ ብንሞክርም ጭራው ሁልግዜ የተቀለበሰ ነው፡፡ (ሳቅ) አያችሁ? ስለዚህ እነዚህ ሰዎች የቁሳዊ ዓለምን ደስታ ይሻሉ፡፡ ስዋሚጂ አንዳንድ ማንትራዎችን በመጠቀም አንዳንድ የዓለማዊ ደስታን ሊሰጣቸው የሚችል ከሆነ ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን ስዋሚጂ እንዲህ ካላቸው ”ይህ ተንኮለኝነት ነው፡፡ አሁን ወደ ክርሽና መመለስ አለባችሁ፡፡ ይህ የምታደርጉት ጥሩ አይደለም፡፡“ ተብለው ከተነገሩ መሸሽ ይጀምራሉ፡፡ ምክንያቱም ጭራውን ሁልግዜ እንደተቀለበሰ መያዝ ሰለሚፈልግ ነው፡፡ ምንም እንኳን ዘይት ብታደርጉበትም ተመልሶ መቀልበሱ አይቀርም፡፡ (ሳቅ) በሽታቸው ይኅው ነው፡፡ የሚፈልጉትም ቁሳዊ ወይንም ዓለማዊ ነገር ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ “በማንትራ ወይንም በተለያዩ ትሪኮች የዓለማዊ ደስታችንን የምንጨምር ከሆነ ይህም በጣም ጥሩ ይሆናል፡፡” ድራግ እንውሰድ እና ወደ ሞኞች ገነት በመግባት እንዲህ እናስብ... “ኦ አሁን በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ነኝ፡፡” በእንደዚህ አስተሳሰብ እራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ በሞኞችም ገነት ውስጥ ገብተው ለመቅረት ይፈልጋሉ፡፡ እኛም ትክክለኛውን ገነት ስናቀርብላቸው አይቀበሉትም፡፡ እሺ አሁን መዘመር እንችላለን፡፡