AM/Prabhupada 0570 - ምንም እንኳን በባል እና በሚስት መሀከል አለመግባባት ቢፈጠርም መፋታት ሊኖር አይገባውም፡፡
Press Interview -- December 30, 1968, Los Angeles
ጋዜጠኛ፡ በህንድ አገር ውስጥ ብዙ የትዳር መፋታት ይታያልን?
ፕራብሁፓድ፡ አዎን በዚህ ዘመን ያሉት ልጆች እና ልጃገረዶች በቀላሉ መፋታትን ይመርጣሉ፡፡ በቀድሞ ግዜ ግን ምንም እንኳን ባል እና ሚስት ቢጣሉ እና በመሀከላቸው ብዙ መስማማትነት ባይኖርም መፋታት ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ የእኔን ሕይወት እራሱ ውሰድ፡፡ እኔም ባለ ትዳር ነበረኩኝ፡፡ አሁን ትዳር ላይ አይደለሁም፡፡ በተግባራዊ ኑሮአችን ከባለቤቴ ጋር ስምምነት አልነበረኝም፡፡ ቢሆንም ግን ለመፋታት ጥያቄ አልነበረንም፡፡ አያችሁ? እሷም ያለመችው ነገር አይደለም እኔም ያለምኩት ነገር አልነበረም፡፡ ይህ ለእኛ የማይታወቅ ነገር ነበረ፡፡ አሁን አሁን ግን ይህ ለሁሉም በመተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡
ጋዜጠኛ፡ አዎን ይህ የምእራባውያን ባህል ነው፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን ትክክል ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡ በህንድ አገር ውስጥ ብዙ ተከታዮች አለህን?
ፕራብሁፓድ፡ አዎን የእኔ እንቅስቃሴ ባይሆንም የእኔ መንፈሳዊ ወንድሞች ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡ ምን ያህል፡፡ ምን ያህል ይሆናሉ?
ፕራብሁፓድ፡ በሚልዮን የሚቆጠሩ ይህም ያቫይሽናቭ ፍልስፍና ወይንም የክርሽና ንቃት በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ እየተከታተሉ ነው፡፡ ወደ 80% ማንኛቸውንም ህንዳዊ ብትጠይቅ ሰለ ክርሽና ንቃት ብዙ ነገር ሊነግርህ ይችላል፡፡ የእኔ ተማሪ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ብዙ መንፈሳዊ ሰዎች ልክ እንደ እኔ በብዛት ይገኛሉ፡፡ የሚያደርጉትም ይህንኑ ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡ አንተስ ስርዓት ያለው ልምምድ አድረገህ ነበር?
ፕራብሁፓድ፡ አዎን ከመንፈሳዊ አባቴ የድቁና ስርዓትን ወስጄአለሁ፡፡ ይህም የመንፈሳዊ አባቴ ፎቶግራፍ ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡ ኦ አየሁት፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን አገርህም ከእኔ መረጃ ወይንም ሰርቲፊኬት ሲፈልጉ ይህም እኔን ነዋሪ ለማድረግ ማለት ነው፡፡ ያንን ግዜ እኔም መንፈሳዊ ጓደኞቼን ጠይቄ የድቁና ስርዓቴን እንደወሰድኩ የሚያሳየውን ሰርቲፊኬት አመጣሁላቸው፡፡ ይኅው ነው፡፡ አለበለዛ ግን በእኛ አገር ምንም ዓይነት ሰርተፊኬት አያስፈልግም፡፡
ጋዜጠኛ፡ ይህም ማለት በህንድ አገር ለዚህ ንቃት እንደ ሴሚናሪ ወይንም ኮርስ ለመከታተል አይኬድም ማለት ነውን? ወዴት ነው ይህንን ኮርስ ወደ ሴሚናሪ ወይንም ገዳም ሂዶ ለአራት ዓመታት ለመከታተል የሚቻለው?
ፕራብሁፓድ፡ አይደለም፡፡ ይህም እራሱ ገዳም ነው፡፡ ገዳማትም አሉ። ድርጅቶችም አሉ፡፡ ጎድያማት የሚባልም ድርጅት በህንድ አገር አለ፡፡ እነርሱም በመቶ የሚቆጠሩ ቅርንጫፎች አሉዋቸው፡፡
ጋዜጠኛ፡አንተም ለተወሰነ የኮርስ ጥናት ውስጥ ተሳትፈህ ነገርን?
ፕራብሁፓድ፡ አዎን የተወሰነ የኮርስ ጥናት አድርጌአለሁ፡፡ ይህም በእነዚህ በሁለት ወይንም በሶስት መፅሀፍቶች የተመሰረተ ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ ማንም ሰው እነዚህን መፅሀፍቶች ማንበብ ይችላል፡፡ ብሀገቨድ ጊታ ሽሪማድ ብሀገቨታም ወይንም ቼታንያ ቻሪታምርታ፡፡ ከነዚህም መፃህፍት ሁሉን ነገር መማር ትችላለህ፡፡ ብዛት ያላቸውንም ብዙ ቮሉዩም መጻህፍትም መማር አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ብሀገቨድ ጊታ በጣም ጥሩ የሆነ ቅዱስ መፅሀፍ ነው፡፡ አንድ መስመር እንኳን ብተረዱ ለመቶ ዓመት የሚሆን ያህል በመንፈሳዊ እርምጃ የዳበራችሁ እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ አየህ? ማለት የፈለግሁትም ይህ ብዙ ትርጉም ያለው እና ጠንካራ መልእክት ያለው ነው፡፡ ስለዚህም ይህንን የብሀገቨድ ጊታ ቅዱስ መፅሀፍ አትመነዋል፡፡ እነዚህም ሕዝቦቻችሁ ይህንን መፅሀፍ ያንብቡ፡፡ ጥያቄም በመጠየቅ ለመረዳት ይሞክሩ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ምን እንደሆነ ለመረዳት ይሞክሩ፡፡
ጋዜጠኛ፡ ማክሚለን ይህንን መጽሀፍ እያተመ ነው፡፡
ፕራብሁፓድ፡ አዎን ማክሚለን ይህንን መፅሀፍ እያተመ ነው፡፡