AM/Prabhupada 0618 - መንፈሳዊ አባይ ይህንን ሲያይ ደስ ይለዋል፡፡ “ይህ ልጅ ከእኔ በላይ በንመፈስ የዳበረ ነው፡፡”



Lecture on CC Adi-lila 7.91-2 -- Vrndavana, March 13, 1974

አንድ ድቁና የወሰደ ተማሪ በመንፈሳዊ አገልግሎቱ ወደፊት የተራመደ ከሆነ የመንፈሳዊ አባቱ በጣም ደስታ ይሰማዋል፡፡ እንዲህም ያስባል "እኔ ስሜት የማይሰጥ ሰው ነኝ፡፡ ነገር ግን ይህ ተማሪ" "ትእዛዜን ተቀብሎ ብዙ ውጤትን አሳይቷል፡፡ ይህ የእኔን ውጤታማኝነት ያሳየኛል፡፡" የመንፈሳዊ አባትም የጋለ ፍላጎት ይኅው ነው፡፡ አባትም ከልጅ ጋር ያለው ግኑኝነት በዚሁ የተመሰረተ ነው፡፡ ማንም ሰው ግን ሌላው ሰው ከእርሱ በላይ የተሻለ ሆኖ እንዲያገኝ አይፈልግም፡፡ በተፈጥሮ ያለን አዝማምያ ይህንን ይመስላል፡፡ አንድ ሰውም በአንድ ነገር ከእኔ የተሻለ ሆኖ ከተገኘ እኔም ወዲያውኑ ምቀኝነት ላሳይ እችላለሁ፡፡ መንፈሳዊ አባት ግን ወይንም የወለደን አባት ምቀኛ ሊሆን አይችልም፡፡ በውስጡም በጣም ደስተኛ ሆኖ ይገኛል፡፡ "ይህ ልጅ ከእኔ በላይ ወደፊት የተራመደ ሆኖ ይታያል" መንፈሳዊ አባት እንዲህ ብሎ የመደሰት ባህርይ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ክርሽና ቼይታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎ ገልጿል፡፡ "እኔ በዘመርኩኝ በደነስኩኝ እና በደስታ ባለቀስኩኝ ቁጥር" "የመንፈሳዊ አባቴ እንዲህ በማለት ያመሰግነኝ ነበረ፡፡" "ብሀላ ሀይላ" ይህ እጀግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ "ፓይሌ ቱሚ ፓራማ ፑሩሳርትሀ" አሁን የሕይወትህን የከፍተኛውን ደረጃ ውጤት አግኝተሀል፡፡ "ቶማራ ፕሬሜቴ" ወደፊትም ብዙ የተራመድክ በመሆንህ "አሚ ሀይላን ክርታርትሀ" እኔ ያንተ ውለተኛ ነኝ፡፡ የመንፈሳው አባት ደረጃ ይህ ነው፡፡ ከዚያም ያበረታታናል፡፡ "ናቻ ጋዎ ብሀክታ ሳንጌ ካራ ሳንኪርታና" "እስከ አሁን ብዙ እርምጃ አድርገሀል፡፡ አሁን በዚሁ ቀጥለበት፡፡" ናቻ "ደንስ" "ጋዎ" ዘምር "ብሀክታ ሳንጌ" ይህም ከድቮቲዎች ጋር በመሆን አለበት፡፡ ሙያን ብቻ ማሳደግ ሳይሆን ብሀክታዎችን በመጐዳኘት አንድ ሰው የመንፈሳዊ ሕይወቱን የተሳካ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ናሮታማ ዳስ ታኩር እንዲህ ይላል፡፡ "ታንዴራ ቻራና ሴቪ ብሀክታ ሳኔ ቫስ ጃናሜ ጃናሜ ሞራ ኤይ አቢላስ" ናሮታማ ዳስ ታኩር እንዲህ ይላል፡፡ "ከትውልድ ትውልድ" ምክንያቱም ድቮቲ (አገልጋይ) ዋናው ትኩረቱ ወደ ቤቱ ወደ አብዩ አምላክ ቤት ለመሄድ አይደለም፡፡ አይደለም፡፡ ያለበት ቦታ ሁሉ ምንም ለውጥ አያመጣም፡፡ ምኞቱ ሁሉ ግን አብዩ የመላእክት ጌታን ለማመስገን እና ለማገልገል ብቻ ነው፡፡ይህ ነው አብዩ ስራው፡፡ ድቮቲ ወይንም ብሀክታ የሚዘምረው የሚደንሰው እና የሚያከናውነው የትሁት አገልግሎት ሁሉ ወደ ቫይኩንትሀ ወይንም ወደ ጐሎካ ቭርንዳቫን ለመሄድ ሰለፈለገ አይደለም፡፡ ይህ የክርሽና ፍላጐት ነው፡፡ "እርሱም ከፈቀደ ይወስደኛል፡፡" ልክ ብሀክቲቪኖድ ታኩር እንደገለፀው፡፡ "ኢቻ ያዲ ቶራ" "ጃንማኦቢ ያዲ ሞር ኢቻ ያዲ ቶራ ብሀክታ ግርሂቴ ጃንማ ሀው ፓ ሞራ" የድቮቲ (አገልጋይ) ፀሎት እንዲህ ነው፡፡ ክርሽናን እንዲህ ብሎ አይጠይቅም፡፡ "እባክህ ወደ ቫይኩንትሀ ወይንም ወደ ጎሎካ ቭርንዳቫና ውሰደኝ፡፡" ብሎ አይፀልይም፡፡ "እንደገና መወለድ አለብህ ብለህ የምታስብ ከሆነ እንደገና ልወለድ፡፡" "የምጠይቅህ ነገር ቢኖር ግን እኔ በድቮቲ (አገልጋይ) ቤት ውስጥ እንድወለድ አድርገኝ" ይኅው ነው ፀሎቱ፡፡ "ይህንንም የምፈልገው እንዳልረሳህ ነው፡፡" ይህ ነው የድቮቲ ፀሎት፡፡