AM/Prabhupada 0012 - የእውቀት ሁሉ መነሻ በማዳመጥ መሆን አለበት፡፡



Lecture on BG 16.7 -- Hawaii, February 3, 1975

እያንዳንዳችን: በሁሉም ነገር የተሟላ ስልት የለንም:: በአይናችን ከመጠን ያለፈ እንኮራለን:: እንዲህም እንላለን "አምላክን ልታሳየኝ ትችላለህ?" እንላለን: ዐይናችን ምን ያህል አማላክን ለይቶ የማወቅ ችሎታ አለውና ነው: "እስቲ አማላክን አሳየኝ“ የምንለው? ሰው ይህን ለይቶ አያስብም: አማላክንም ለይቶ የማወቅ ችሎታም የለውም: ቢሆንም ግን: “አምላክን አሳየኝ” ብሎ ይጠይቃል: እነዚህ ዐይኖቻችን:ለማየት ብዙ ነገር ማስተካከል ያስፈልጋቸዋል: አሁን መብራት ስለ አለ ለማየት ትችላላችሁ: መብራት ከጠፋ ግን: ምንም ነገር ማየት አትችሉም: ታድያ እንደዚህ አይነቱ ዐይን ፍፁምነቱ ምን ላይ ነው? ከዚህ ግድግዳ ጀርባ እንኳን የሚደረገውን ለማየት ያዳግተናል: ስለዚህም በተፈጥሮ ያለንን የስሜት የሰውነት ክፍሎች:ፍፁም ለሆነ እውቀት መነሾ ይሆናሉ ብለን መተማመን የለብንም: የእውቀት መነሾ ከማዳመጥ መሆን አለበት:ይህም “ሽሩቲ” ይባላል: በዚህም ምክንያት: የቬዳዎች ስም:“ሽሩቲ:ሽሩቲ ፕራማና" ይባላል: ልክ ልጅ አባቱን ለማወቅ እንደሚጥር ሁሉ: ይህስ ልጅ እንዴት ነው ስለ አባቱ ለማወቅ የሚችለው?መረጃውም ከ ”ሽሩቲ“ ነው:ይህም ከእናቱ ስለ አባቱ ማንነት በማዳመጥ ነው: እናት: ”ይህ አባትህ ነው“ ማለት ትችላለች: እንደዚህም ሁሉ በማዳመጥ: ይረዳል እንጂ: አባቱ እንዴት ሊሆ ን እንደቻለ ለማየት አይችልም: ልጁ ከመወለዱ በፊት አባቱ በህይወት ስለነበረ: ልጁ አባቱ እንዴት እንደተፈጠረ ሊረዳ አይችልም: እንደዚሁም ሁሉ: በማየት ብቻ:ፍፁም የሆነ እውነትን ለማረጋገጥ አይቻልም: ከባለ ስልጣን መስማት አለብን:እናት ባለ ስልጣን ናት: ስለዚህም ”ሽሩቲ ፕራማና“ መረጃችን ማዳመጥ ነው እንጂ ማየት አይደለም: እነዚህ ፍፁም ያልሆኑ አይኖቻችን:ለማየት ብዙ እንቅፋቶች አሏቸው: እንደዚሁም ሁሉ:በቀጥታ በማየት:ትክክለኛ እውነትን ሁልግዜ ለማግኘት አንችለም: ቀጥታ ማየት ግምት ሊሆን ይችላል:ልክ እንደ ”ዶክተር እንቁራሪት“ ታሪክ ማለት ነው: ”ዶክተር እንቁራሪት“ ስለ አትላንቲክ ውቅያኖስ ግምት ውስጥ ገባ: 3 ሜትር ኩሬ ውስጥ ተቀምጦ: ጓደኛው እንዲህ አለው: ”እኔ ትልቅ ውቅያኖስን አይቻለሁ” አለው: ይህ ውቅያኖስ ማን ይባላል ብሎ ዶክተር እንቁራሪት ጠየቀ:ጓደኛውም “አትላንቲክ ይባላል” ብሎ ነገረው: ምን ያህል ትልቅ ቢሆን ነው ብሎ ጠየቀ: ዶክተር እንቁራሪትም “ምንአልባት አራት ሜትር ይሆን” ብሎ ያስባል: ”ይህ ትልቁ ውቅያኖስ የምትለው: ምናልባት 3 ሜትር ወይንም 4 ሜትር ወይንም 5 ሜትር ስፋት ያለው ሊሆን ይችላል“ብሎ ተናገረ: በል እንጂ ተናገር: ማናልባት 10 ሜትር ስፋት? እና በእንደዚህ በመሰለ ግምት:አትላንቲክ እና ፓሲፊክ ውቅያኖስን እንዴት አድርጎ ዶክተር እንቁራሪት ሊረዳ ይችላል? የአትላንቲክ እና የፓስፊክ ውቅያኖስን ስፋት በግምት ለማወቅ ትችላላችሁን? እንደዚሁም ሁሉ በግምት ትክክለኛ እውቀት ማግኘት አይቻልም: ሳይንቲስቶች ይኅ ህዋ ምን ያህል ኮከቦች እንዳሏት ለመረዳት ለብዙ አማታት ይገምቱ ነበር: የህዋስ ስፋቱ ምን ያህል ነው? ስለ ገዛ ምድራችን እንኳን ብዙ የማናውቀው ነገር አለ: ስለመንፈሳዊው አለሙ ይቅርና: ያ ከአቅማችን በላይ ለመረዳት የራቀ ነው: “ፓራስ ታስማት ቱ ብሃቮ ንዮ ቭያክቶ ቭያክታት ሳናታና” (ብ ጊ 8 20) በ ብሃገቫድ ጊታ የቅዱስ መጽሃፍ ውስጥ ሌላ መንፈሳዊ አለም እንዳለ ተገልጿል: ይህ ፍጥረት የምታዩት: በሰማይ የተከበበ: ከዚህ ከምናየው በላይም: አምስት የተደራረቡ ፍጥረታት አሉ: ልክ እንደ ኮኮናት ፍሬ: የተደራረበ ሽፋን በሰማይም ይገኛል: ጠንካራ የሆነ ሽፋን አለ: ከዚህም ውስጥ ውሃ ይገኛል: በዚህም ሽፋን ውስጥ: እና በውጭ በሚገኘው ሽፋን ውስጥ:ሌላ አምስት አይነት ሽፋኖች አሉ:እነዚህም ከሌሎቹ በጣም ትልቅ ሁነው ይገኛሉ: የውሃ ሽፋን አለ:የአየር ሽፋን አለ: የእሳት ሽፋን አለ:እና እነዚሁን ሁሉ ጥሶ ማለፍ ያስፈልጋል: ከዚያም ወደ መንፈሳዊ አለም መድረስ ይቻላል: እነዚህም ህዋዎች: ቁጥራቸው ሊገመት የማይችል ነው:“ኮቲ” “ያስያ ፕራብሃ ፕራብሃቮ ጃጋድ አንዳ ኮቲ” (ብ ሰ 5 40) “ጃጋድ አንዳ” ማለት ህዋ ማለት ነው: “ኮቲ” ማለት: በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ:በአንድነት ማለት ነው:ይህም የምድራዊ አለም ነው: ከዚህም ምድራዊ አለም ባሻገር:የመንፈሳዊ አለም ይገኛል: ያም ሰማይ ነው: የሚባለውም “ፕራቭዮማ” ነው: እንደዚህም ሁሉ: በስሜታችን በመረዳት:በጨረቃ እና በፀሃይ ያለውን ገምተን ለመረዳት አንችለም: ይህች ፕላኔት:በዚህ ህዋ ውስጥ የምትገኝ: እንዲሁም: እንዴት ብላችሁ የመንፈሳዊ አለምን በግምት ልትረዱ ትችላላችሁ?ይህ ሞኝነት ነው: ስለዚህም ”ሻስትራ“ (ቅዱስ መጽሐፎች) እንዲህ ትላለች “አቺንትያ ክሀሉ ዬ ብሃቫ ና ታምስ ታርኬና ዮጃዬት” “አቺንትያ” ማለት ሊረዱት የማይቻል: ከስሜታዊ መረጃዎቻችን የራቁ: በክርክር ሊረዱት የማይቻል ስለሆነ:ግምት ውስጥ አትግቡ: ይህም ሞኝነት ነው:በዚህም መንገድ መረዳት አይቻልም: ስለዚህ ወደ መንፈሳዊ አስተማሪያችን መሄድ አለብን: “ታድቪግናናርትሃም ሳ ጉሩም ኤቫብሂቼት ሳሚት ፓኒህ ሽሮትሪያም ብራህማ ኒሽትሃም (ም ዩ 1 2 12) ይህ ነው ስርአተ ጉዞው: