AM/Prabhupada 0350 - ጥረታችንም ሁሉ የሰው ልጅ ክርሽናን ለማየት እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡



Lecture on BG 7.2 -- Nairobi, October 28, 1975

ብራህማናንዳ፡ ከቬዲክ ስነፅሁፎች እንደምንረዳው ክርሽና ወሰን እንደሌለው እንረዳለን፡፡ በተለይ የራስ ሊላውን ዳንስ ከጐፒዎቹ ጋር ሲያደርግ እና ክርሽና ወሰን የሌለው ከሆነ ለምን እንዲህ አላደረገም...?

ህንዳዊ ሰው፡ ለምን ክርሽና ሁሉም ነፍሳት ወደ መንፈሳዊ ዓለም እንዲመለሱ እራሱን በመላ ዓለም በማቅረብ እኩል ዕድል አይሰጣቸውም?

ብራህማናንዳ፡ ለምን ክርሽና ሁሉም ነፍሳት ወደ መንፈሳዊ ዓለም እንዲመለሱ እራሱን በመላ ዓለም በማቅረብ እኩል ዕድል አይሰጣቸውም?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን በመላ ዓለም እራሱን እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ነገር ግን አንተ እርሱን የሚያይ ዓይን የለህም፡፡ ይህ ነው የአንተ ጉድለት፡፡ ክርሽና በሁሉም ቦታ እራሱን ከስቶ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ፀሀይ በሰማይ ላይ ተከስታ ትገኛለች፡፡ ታድያ ለምንድነው ለማየት የማትችለው? መልስህ ምንድን ነው? ፀሀይ በሰማይ የሌለች ይመስልሀልን? ፀሀይ የሌለች ይመስልሀልን? ወደ ጣራ ላይ ውጣ እና ፀሀይን ለማየት ሞክር፡፡ (ሳቅ) አንተ ተንኮለኛ ለምን ፀሀይ የለችም ብለህ መረጃ አቀረብክ? “የለችም የለችም ፀሀይ የለችም፡፡” ይህንን የተማሩ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉን? ፀሀይንም ለማየት ባለመቻልህ ፀሀይ የለችም ማለት ነውን? ይህስ በተማሩ ሰዎች ተቀባይነት ሊያገኝ ይቻላልን? ማታ ማታ ፀሀይ ለዓይናችን አትታይም፡፡ ታዳያ ለተማረ ወይንም ሰለተፈጥሮ የሚያውቅን ሰው ብትጠይቁት “የለችም የለችም ፀሀይ የለችም“ ብትሉት ሊቀበለው ይችላልን? መልስ የሚሰጣችሁም እንዲህ በማለት ነው፡፡ ”አንተ ተንኮለኛ ፀሀይ ሁል ግዜ አለች ነገር ግን አንተ ሁልግዜ ልታያት አትችልም፡፡“ ይኅው ነው፡፡ ”ከተንኮለኛነትህ መውጣት ብቻ ነው የሚያስፈልግህ፡፡ ከዚያም ሀቁን ለማየት ትችላለህ፡፡“ ”ናሀም ፕራካሻህ ሳርቫስያ ዮጋ ማያ ሳማቭርታሀ“ (ብጊ፡ 7.25) ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ ለተንኮለኞች እራሱን ግልጽ አያደርግም፡፡ የመንፈሳዊ እውቀት ያለው ግን ለማየት ይችላል፡፡ ፕሬማንጃና ቹሪታ ብሀክቲ ቪሎቻኔና ሳንታሀ ሳዳይቫ ህርዳዬሹ ቪሎካያንቲ ያም ሽያማሱንዳራም አቺንትያ ጉና (ብሰ፡5.38) የአብዩ አምላክ ትሁት አገልጋዮች ክርሽናን ሁሌ እንደአዩት ነው፡፡ ለእነርሱም ሁልግዜ እንደተከሰተ ነው፡፡ ለተንኮለኞች ደግሞ ሊታይ አይችልም፡፡ ይህ ነው ልዩነቱ፡፡ ስለዝህ ከተንኮለኝነት መውጣት አለባችሁ፡፡ ከዚያም ክርሽናን ለማየት ትችላላችሁ፡፡ ኢሽቫራ ሳርቫ ብሁታናም ድርዴሼ አርጁና ቲስትሀቲ (ብጊ፡ 18.61) በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ክርሽና ይኖራል፡፡ ነገር ግን ይህን ታውቃላችሁን? ማየትስ ትችላላችሁን? መነጋገርስ ትችላላችሁን? እርሱም በልባችሁ ውስጥ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከማን ጋር ነው የሚነጋገረው? "ቴሻም ሳታታ ዩክታናም ብሀጃታም ፕሪቲ ፑርቫካም ዳዳሚ ቡድሂ ዮጋም ታም” (ብጊ፡ 10.10) የሚነገገረውም 24 ሰዓት በእርሱ ትሁት አገልግሎት ከተሰማሩት ትሁት አገልጋዮቹ ጋር ነው። ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጿል፡፡ ብሀገቨድ ጊታን አታነቡምን? ሰለዚህ ሁሉም ነገር ብቁነት ያሰፈልገዋል፡፡ የዚህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ዓላማ ሰዎች ክርሽናን ለማየት ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡ ብቁ ሳንሆን እንዴት አድረገን ለማየት እንችላለን? ይህ ብቁነት ያስፈለገዋል፡፡