AM/Prabhupada 0355 - የምንገረው ነገር ሁሉ አብዮታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው፡፡



Lecture on SB 5.5.1-8 -- Stockholm, September 8, 1973

”ካማን“ ማለት በህይወት የሚያስፈልጉን ነገሮች ሁሉ ማለት ነው የሚያስፈልጋችሁንም ነገር ሁሉ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ: መሬት በማረስ:እህል ይገኛል:ከላም ወተት ይገኛል: ይህ ነው:ይህ በቂ ነው: ነገር ግን መሪዎቹ ፕላን እያደረጉልን ነው:በግብርናቸው ከተደሰቱ ማን በፋክተሪ ውስጥ ይሰራል:ብለው ያስባሉ: ትንሽ እህል እና ወተት ካገኙ:ማን ፋክተሪ ውስጥ ይሰራል? ስለዚህም ታክስ ያደርጋሉ:እንደዚህም ቀላል ኑሮ መኖር ያዳግታል:ይህ ነው ሁኔታው: ኑሮን ለማቅለል ብትፈልጉም:የግዜው መሪዎች አይፈቅዱላችሁም: እንደ ውሻ:አሳማ እና አህያ:እንድትሰሩ ይመኛሉ:ይህ ነው ሁኔታው: ቢሆንም ከዚህ አሰፈላጊ ጥረት ግረት መራቅ አለብን: መንግስት እኔ ላይ እርምጃ ሊወስድ ይችላል እንደዚህም ስለተናገርኩ:ይህም አብዮታዊ አነጋገር ነው: አዎን:ግን ይህ እውነት ነው:አንድ ሰው ለምን ጥረት ግረት ውስጥ ይገባል? አምላክ ለሁሉም አቅርቧል:ለወፎች:ለአውሬዎች:ለእንስሳዎች:ለጉንዳኖች:እኔስ ለእርሱ አገልጋይ ከሆንሁኝ:ለምንድን ነው እህል የማይሰጠኝ? ምን ስህተት ሰራሁ?ስለዚህ በዚህ ሃሳብ አትረበሹ: የሚያስፈለጋችሁን ነገር በሙሉ:አምላክ ያቀርብላችኋል:ከእናንተ የሚጠበቅባችሁ ግን:ስለ ክርሽና ንቃታችሁ ወስናችሁ ወደ ፊት መራመድ አለባችሁ: በዚህ ሰሜት በማይሰጥ እምነት አትረበሹ:አመሰግናለሁ: